ሀገሬ ቲቪ

ዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ቀን

ዓለም ላይ በየዓመቱ 600 ሚሊዮን የሚጠጉ ምግብ ወለድ ህመሞች የሚከሰቱ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በየዓመቱ ከሚሞቱ 420 ሺሕ ሰዎች መካከል 125 ሺሕ የሚሆኑት ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ በ2018 ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የምግብ ደህንነት ቀን በየዓመቱ ግንቦት 30 እንዲከበር ወስኗል፡፡

ዘንድሮ ደህንነቱ የተጠበቀ ምግብ፣ ለተሻለ ጤና በሚል መሪ ቃል የሚከበረው ዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ቀን ምግብ ወለድ ስጋቶችን መከላከል፣ መለየት እና መቆጣጠር የሚያስችሉ ሥራዎች ትኩርት አግኘተው እንዲሰሩ በማበረታታት የምግብ ዋሰትና መረጋገጥ፣ ጤና፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣ ግብርና፣ የገበያ ትስስር፣ ቱሪዝም እና ዘላቂ ልማት ላይ አሰተዋፆ ማበረከትን ዓላማው አድርጓል፡፡

ምግብ ወለድ በሽታዎች በአብዛኛው ተላላፊና አደገኛ ሲሆኑ ባክቴሪያ፣ ቫይረስ፣ ጥገኛ ተውሳኮች ወይም አደገኛ ንጥረ ነገሮች ከተበከለ ምግብ ወይም ውሃ ጋር ወደ ሰውነታችን ሲገቡ የሚከሰቱ ናቸው፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-07