በናይጄሪያ የቢያፍራን ተገንጣይ ቡድን አማካኝነት የሚወጡ የፌስቡክ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ ትሥሥር መድረኮች የሚወጡ ጽሁፎችን ገደብ ይጣልልኝ ሲል የናይጄሪያ መንግሥት አስታውቋል።
የቢያፍራን ተገንጣይ የቡድን አባላት የማህበራዊ ሚዲያ ትሥሥር መድረኮች ተጠቅመው ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስና በሀገሪቱ ውስጥ የዘር ጥላቻን ለመፍጠር ቢጠቀሙበትም የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጽ ድርጅቶች ግን ይህን አሉታዊ ድርጊት ለመከላከል ሲሰሩ አይታዩም ሲል ተችቷል።
የሀገሪቱ የኢንፎርሜሽን እና የባሕል ሚኒስትሩ ላኢ መሀመድ ቡድኑ በናይጄሪያ መንግስት በአሸባሪነት የተፈረጀ እንደሆነ ጠቅሰው ፌስቡክና ሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ለእነዚህ አሸባሪዎች ልቅ የሚያደርግበት ምክንያት ትክክል አይደለም ማለታቸውን አፍሪካን ኒውስ ጽፏል።
በሌላ በኩል ንቅናቄው ከናይጄሪያ ነፃ የሆነች ቢያፍራ የተባለች ሀገር እንድትፈጠር የሚታገል ተገንጣይ ቡድን መሆኑ ታውቋል።ትችት ስለቀረበባቸው የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች ላይ ዘገባው ያለው ነገር የለም።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-07
