ራያን ኤር አየር መንገድ በደቡብ አፍሪካውያን ላይ የቋንቋ ፈተና በማዘጋጀት ማጠናቀቅ ያልቻሉት መንገደኞች እንዳይጓዙ እና የከፈሉት ገንዘብ እንዲመለስ እያደረገ ነው፡፡
ከአውሮፓ ግዙፉ የአጭር ርቀት አየር መንገዶች መካከል የሆነ ራይን ኤር በደቡብ አፍሪካ 12 በመቶ ሕዝብ ብቻ የሚናገረውን ቋንቋ ለፈተና አቅርቧል፡፡
የደቡብ አፍሪካ ደንበኞች ወደ በረራ ከመግባታቸዉ በፊት ዜግነታቸውን ለማረጋገጥ ‹‹የአፍሪካንስ›› ቋንቋ ፈተና መውሰድ አለባቸው ማለቱ የዉዝግብ መነሻ ሆኗል፡፡
ፈተናው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንቱ ማናቸዉ፣ ዋና ከተማዋስ እንዲሁም አሽከርካሪዎች በቀኝ ወይስ በግራ መንገድ ያሽከረክራሉ የሚሉ ጥያቄዎችን ያካትታል፡፡
የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ “ከፍተኛ የተጭበረበሩ የደቡብ አፍሪካ ፓስፖርቶች በመኖራቸዉ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ያለመ ፈተና ነው” ሲሉ ተከላክለዋል፡፡
ሀገሪቱ 11 ይፋዊ የሥራ ቋንቋዎች እያሏት ራያን አየር መንገድ ለምን አፍሪካንስን እንደለየ ግልጽ አልሆነም በሚል አስተችቶታል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-07
