አፍሪካ ከዩክሬን የምታገኘውን ስንዴ ለመተካት አይኖቿን ወደ ጃፓን ልታዞር ትችላለች ተባለ፡፡የተባበሩት መንግሥታት ረዳት ዋና ፀሃፊ አሁና ኢዚያኮንዋ በጃፓን የአምስት ቀናት ተልዕኮ ካደረጉ በኋላ የአፍሪካ ሀገራት በሩስያ እና በዩክሬን የምግብ ምርቶች እጥረት የተፈጠረውን ክፍተት መሙላት ከተለመደው የኢኮኖሚያዊ ዕርዳታ ውጪ መመልከት አለባቸው ብለዋል፡፡
ኢዚያኮንዋ ከረዳት ዋና ፀሃፊነታቸው በተጨማሪ የመንግሥታቱ የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የአፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ሲሆኑ በጃፓን ያሉ የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ አጋሮች ለአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ጃፓን በመላው አፍሪካ የሩዝ ምርትን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ከ2008 ጀምሮ በአፍሪካ ሩዝ ልማት ቅንጅት (ሲአርዲ) የተጀመረውን የሦስት-ደረጃ መርሃ ግብር ስትሰራ ቆይታለች፡፡በ2022 ነሐሴ 27 እና 28 በቱኒዚያ ሊካሄድ በታቀደው ስምንተኛው የቶኪዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት ኮንፈረንስ ላይ በጃፓን እና በአፍሪካ መካከል ተጨማሪ ትብብሮች እንደሚኖሩ ሬድዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል ዘግቧል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-08
