ቻይና ወደ ጨረቃ፣ ማርስ እና ከዚያም በላይ ለመሄድ አቅዳለች ይለናል ቢቢሲ ያስነበበው መረጃ፡፡ሦስት ቻይናውያን የጠፈር ተመራማሪዎች በሀገሪቱ አዲስ የጠፈር ጣቢያ ላይ ለመስራት የስድስት ወራት ተልዕኮ ጀምረዋል፡ይህ እርምጃ ሀገሪቷ ለሚቀጥሉት አሥርት ዓመታት ራሷን የህዋ ኃይል መሪ ለማድረግ የተወሰደ ነው፡፡
ባለፈው ዓመት ቻይና የቲያንጎንግ ወይም "ሰማያዊ ቤተ መንግሥት" የህዋ ጣቢያዋን የመጀመሪያውን ክፍል ወደ ምህዋር ልካለች፤ በዓመቱ መጨረሻ እንደ ሜንግቲያን ሳይንስ ያሉ የምርምር ተቋማትተጨማሪ ክፍሎችን ለመጨመር አቅዳለች፡፡የቻይና ምኞት በዚህ ብቻ አያበቃም ፤እ.ኤ.አ. በ2030 የመጀመሪያዎቹን ጠፈርተኞች በጨረቃ ላይ ለማስቀመጥ እና ከማርስ እና ጁፒተር ናሙናዎችን ለመሰብሰብ ምርመራዎችን ለመላክ ጭምር ታቅዷል፡፡
ቻይና ሦስቱ ጠፈርተኞች ወደ ህዋ በማስገባት ብሎም አዲስ የጠፈር ጣቢያን በመገንባት ከሩሲያ እና ከአሜሪካ ቀጥላ በታሪክ ሦስተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-08
