ሀገሬ ቲቪ

አሰሪና ሰራተኛን የሚያገናኘው መድረክ

የሰው ሀብት ልማት ባለሞያዎች ማህበር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ስላዘጋጀው የስራ አውደርዕይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

አውደርዕይው በኢትዮጵያ ስራ አጥ ዜጎች ከአሰሪዎች ጋር የሚገናኙበት ሲሆን ከሰኔ ሶስት እስከ ሰኔ አምስት በኤግዚቢሽን ማዕከል ይዘጋጃል ተብሏል።

በአውደ ርዕይ ላይ ከ 7000 እስከ 10,000 የሚደርሱ ስራ ፈላጊዎች ከ አሰሪዎች ጋር ለመገናኘት የሚሳተፉ ሲሆን ወደ 30 የሚደርሱ መንግስታዊ የሆኑና ሌሎች የግል ድርጅቶች ሰራተኞችን ለመቅጠር ያላቸውን ክፍት ቦታዎች ማስገባታቸውን የሰው ሀብት ልማት ባለሞያዎች ማዕበር የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ግሩም ከተማ ነግረውናል።

የስራ አጥ ዜጎች ቁጥር በመዲናችን አዲስ አበባ ቢበዛም በክልል ከተሞች ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ መጥቷል። በመዲናዋ የሚዘጋጁ የስራ አውደርዕዮችን ለመካፈል እድል ለማያገኙ የክልል ነዋሪዎች ምን የታሰበ ነገር አለ ስንል ለጠየቅናቸው ጥያቄ አቶ ግሩም ወደክልል ለማሳደግ በስፋት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመዲናዋ እንዲሁም በክልል ከተሞች የሚገኙ ስራ አጥ ዜጎች በኤግዚቢሽን ማዕከል ከ ሰኔ ሶስት እስከ ሰኔ አምስት በሚካሔደው አውደርዕይ በመሳተፍ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-06-08