በዘመነ ኦባማ አሜሪካ እና ቻይና የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር መሳሪያ መታጠቅ በጋራ ሊቃወሙ ተስማሙ። ይህ ሁነት የሆነው በ2005 በዛሬዋ እለት ነበር። ይሁንና ግን ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ትጥቋን እያፈረጠመች እስካሁን ቆይታለች። የዛሬው እለቱን ከታሪክ ትኩረቱን ከሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ባለቤትነት ጉዞ ላይ ያደርጋል።
በ2005 የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማ ከቻይና ጋር የነበራቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማሻሻል በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። የሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር የመታጠቅ ጉዞ ለሃያላኑ ሃገራት የሚዋጥ አልሆነላቸውም። ዋሽንግተን ከቤጂንግ ባደረጉት ስምምነት የፕዮንግያንግን የኒውክለር ትጥቅ ሊያስፈቱ ከስምምነት ደርሰው ነበር። ኒውክሌር የታጠቀችውን ሰሜን ኮሪያን ሊቀበሉ እንደማይችሉም እንዲሁ ገልጸው ነበር። ከዚያ ወዲህም ከዚያ በፊትም ብዙ ስምምነቶች ቢደረጉም ሰሜን ኮሪያን ግን አላስቆሟትም።
በቀጠናው የካፒታሊዝም እና ኮሚኒዩዝም መራኮት የአሜሪካን ጣልቃ ገብነት ተከትሎ ኮሪያን ወደ ካፒታሊስት ደቡብ ኮሪያና ኮሚዩኒስት ሰሜን ኮሪያነት ለሁለት ሰንጥቋታል።
ከወደ ሃያላኑ ደጋግሞ ተቃውሞ የገጠመው የሰሜን ኮሪያ ኒውክሌር የመታጠቅ ጉዞ ከ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኋላ የተጀመረ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዙሪያዋ ካለው አለም ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር ሰሜን ኮሪያ ለደህንነቷ ዋስትና ኒውክሌር ላይ አይኗን እንድትጥል ምክንያት ሆኗል።
ሶቭየት ህብረት የሰሜን ኮሪያ ተመራማሪ እና ኢንጂነሮችን በኒውክሌር ቴክኖሎጂ ላይ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረጓ የወደፊት የሰሜን ኮሪያን የኒውክሌር እድገት መነሻ እንደሆነም ይነገራል።
ኮሚዩኒስት ሰሜን ኮሪያ ከሶቭየት ህብረት በ1950ዎቹ መጀመሪያ አንድ የወዳጅነት ስምምነት አደረጉ። ይሄው ስምምነት ለሰሜን ኮሪያ መሰረታዊ የኒውክሌር ስልጠናን እና ቴክኖሎጂን የሚያቀርብ ነበር።
ሰሜን ኮሪያ የዮንግብዮን የኒውክሌር ምርምር ማእከልን አጠናቀቀች።
ሶቭየት ህብረት መሰረታዊ የኒውክሌር ቁሳቁሶችን ለሰሜን ኮሪያ መሸጥ እና ማቅረቧን ቀጠለች። በ1950ዎቹ መጨረሻ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር የማበልጸግ ሙከራዋን በዮንግብዮን ማእከል ጀመረች።
የኒውክሌር ማምረት ጉዞን ስራዬ ብላ የተያያዘችው ሰሜን ኮሪያ በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ከሶቭየት ህብረት እና ቻይና የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እገዛን ብትጠይቅም ሃያላኑ ጥያቄዋን ውድቅ አደረጉባት። ሃገሪቱ ግን የኒውክሌር ጉዞዋን ቀጠለች።
በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1985 ሰሜን ኮሪያ ለኒውክሌር ሃይል ማመንጫ ተስማሚ የሆነ ነዳጅን በማምረት ቢጫ ኬክ (yellow cake) ተብሎ የሚጠራውን ዩራኒየምን ለማጣራት የሚያስችል ፋብሪካን በዮንግቢዮን ገንብታ አጠናቀቀች።
በዚያው አመት ኒውክሌርን ያለ ማስፋፋት ስምምነትን (Nuclear Non-Proliferation Treaty)ን ተቀበልኩ አለች። ግና ደግሞ የሁለተኛዋን የኒውክሌር ማብላያ ግንባታዋን ቀጠለች። ኒውክሌርን ያለማስፋፋት ስምምነቱን በፈረመች በአራት አመቱ አሜሪካ ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መሳሪያ እቅድ እንዳላት ጠንካራ የሳታላይት መረጃ ምስል አለኝ ስትል ከሰሰቻት።
ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እቅዷን ለማሳደግ የሶቭቭየት ተመራማሪዎችን ለመቅጠር ብታስብም እቅዱን የሰማችው ሶቭየት ህብረት ተመራማሪዎቿን አሰረች።
በሰሜን ኮሪያ ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እቅድ አላት የሚሉ ወቀሳዎች ተጀመሩ። ሰሜን ኮሪያ ለአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ አጄንሲ ሪፖርት አቀረበች። ይሁንና ግን ሪፖርቷ ከአለም አቀፉ የኢነርጂ አጄንሲ ትንተና ጋር የሚቃረን ሆኖ ተገኘ።
የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ተቆጣጣሪዎችን የኒውክሌር ቆሻሻ ማጠራቀሚያዎችን እንዳያገኙ በመከልከል ኒውክሌር ካለማስፋፋት ስምምነቱ መውጣቷን በ1985 ይፋ አደረገች።
በዚያው አመት የመጀመሪያውን ኖዶንግ - 1 የተሰኘ የሚሳኤል ሙከራዋን አደረገች። በጃፓን ባህር ብዮይ ላይ ኢላማውን ያደረገው ይሄው ሙከራ የሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎች ለኢራን እንዲሸጡ በር ከፍቷል።
ይሄው በመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ሰንግ የተጀመረው የሰሜን ኮሪያ ኪም ሰንግ የተጀመረው የኒውክሌር ጉዞ ከርሳቸው ህልፈት በኋላም በልጃቸው በኪም ጆንግ ኡንም ቀጥሏል። በተደጋጋሚ በተለይም አሜሪካ የሰሜን ኮሪያን የመሬት ስር ኒውክሌር የማብላላት ተግባር በሳታላይት መረጃዎች በመታገዝ ብታጋልጥም ተደጋጋሚ ጠንከር ያሉ ማእቀቦችን ሃገሪቱ ብታስተናግድም አሻፈረኝ በማለት አውዳሚ የሆነው የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤትነት ጉዞዋን ቀጥላለች። በግልጽም ሙከራዎቿን ታደርጋለች። አሁን ላይ እስከ 50 የሚደርሱ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች እንዳሏት ይነገራል።
በአብርሃም በለጠ
2022-06-09
