ሀገሬ ቲቪ

የዳግም ምዝገባ ያላደረጉ ድርጅቶች ሊቀጡ ነው

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአንድ ሀገር ውስጥ ያላቸው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም። በሀገራችን ኢትዮጵያም በዘርፉ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶች አሉ።

እነዚህን ድርጅቶች በበላይነት ይቆጣጠር ዘንድ የተቋቋመው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ላለፉት ሦስት ዓመታት ሳከናውናቸው ነበሩ ባላቸው ተግባራቶች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

ቀድሞ የነበረውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ከመቀየር አንስቶ ውስጣዊ የሆነ አደረጃጀቴም ላይ መታደሶችን ማድረጌን እወቁልኝ ብሏል።

በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ከ4 ሺህ የሚበልጡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይገኛሉ። እነዚህ ድርጅቶች በ2011 ዓ.ም ተሻሽሎ በወጥው አዋጅ መሰረት ዳግም ምዝገባ ማድረግ ቢኖርባቸውም ሳያደርጉ ቀተዋል።

በአዋጁ ላይ እንደተቀመጥው ከሆነ ድርጅቶችቹ አዋጁ ከወጣበት መጋቢት 3 2011 ዓ.ም ጀምሮ ባለው አንድ ዓመት ውስጥ የዳግም ምዝገባ እንዲያደርጉ ያዛል።

በውል ከሚታወቁት የሲቪል ድርጅቶች ውስጥ ወደ 1,700 የሚሆኑት ይህንን የዳግም ምዝገባ አላደረጉም ለዚህም መረጃዎች አለመድረሳቸውን እንደምክኛት ያነሳሉ ያሉት የሲቪል ማህበረሰብ ድርግቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ተቋማቸው ለሲቪክ ድርጅቶች መረጃዎች እንዲደርሱ የአቅሙን ስለማድረጉ አንስተዋል።

“የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ለምን የዳግም ምዝገባውን አላደረጉም የሚለውን ስንፈትሽ መረጃዎች አልደረሱንም የሚል ምላሽ ነው ያገኘነው። ነገር ግን ባለስልጣኑ ባሉት የሚዲያ አማራጮች ሁሉ መረጃዎችን ለማድረስ ሞክሯል። ማንኛውም ሰው አዋጆች ከወጡ በኋላ የማወቅ ግዴታ አለበት።”

የመመዝገቢያ ግዜው ካለፈ በኋላ መጨረሻቸው ምን ይሆናል የሚለውን አዋጁ ግልፅ አለማድረጉ ለአሰራር አስቸጋሪ አድርጎት እንደነበር ጠቅሰው፤ የምዝገባ ግዜው ካበቃ በኋላ ከ170 የሚልቁ ድርጅቶች የዳግም መዝግቡን ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ተናግረዋል።

እነዚህንም ድርጅቶች በተለየ መንገድ ሲከታተሏቸው እንደነበር በማንሳት።

“የዳግም ምዝገባው የግዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የመጡ ድርጅቶችን በተለየ መንገድ ለመከታተል ሞክረናል። የድጋፍ ደብዳቤዎችን በማዘጋጀት ስራቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ እና አስቀድሞ ከነበራቸው የባንክ አካውንት ውጪ ሌላ እንዳይከፍቱ በማድረግ። ብሎም በአካውንታቸው ያለውን ገንዘብ እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው የሚያሳይ መመሪያን በማዘጋጀት እንዲተገብሩት ተደርጓል።”

ከዚህ ቀደም የነበሩ መጓተቶችን ያስቀራል የተባለለት ደንብ በሚንስተሮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ስራ መገባቱን ሰምተናል።

በዚህ ደንብ መሰረት የምዝገባ ግዜ ያለፈባቸው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች 3 ሺሕ ብር መቀጮ በመክፈል ምዝገባውን ማድረግ ይችላሉ ነው የተባለው።

በመቀጮ ምዝገባ የሚደረግበት የግዜ ገደብ እስከ መቼ ነው የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ተጨማሪ ደንብ ተዘጋጅቶ ወደ ሚንስሮች ምክር ቤት መላኩንም ከመድረኩ ሰምተናል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-06-09