ኢትዮጵያዊቷ ጸሐፊ ሃና ጊዮርጊስ ለሥመ ጥሩ የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ ሽልማት መታጨቷ ሰማን፡፡
ኢትዮጵያዊ አሜሪካዊቷ ሃና ጊዮርጊስ ዘ አትላንቲክ የተሰኘው ታዋቂው የአሜሪካ መጽሔት ጸሐፊ ስትሆን ፤ በኒውዮርክ ታይምስ፣ ዘ ጋርዲያን እና ሌሎች የህትመት ሥራዎች ላይ በምታሰፍራቸው ጥልቀት ባላቸው የፖለቲካ፣ የባህልና ማኅበራዊ ጽሑፎቿ እውቅናን አግኝታለች፡፡
ለዚህ ሽልማት የታጨጭው ‹‹ኤ ደብል ኤጅድ ኢንኸሪታንስ ›› በተሰኘው አጭር ልብ ወለድ ሲሆን ፤በእጩነት ለቀረቡት ጸሐፊያን ለእያንዳንዳቸው 630 ዶላር ይሰጣቸዋል፡፡
ከሃና በተጨማሪ ከኬንያ ፣ናይጄሪያ እና ከጋና ለእጩነት የቀረቡ ጸኃፊያን በተገኙበት ሐምሌ 26 በለንደን ሙዚየም በሚካሄደው የሽልማት መርሃ ግብር ላይ አሸናፊው ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ባለፈው ዓመት በዚሁ የሽልማት ኢትዮጵያዊቷ ሜሮን ሐደሮ የኬን የአፍሪካ ሥነ ጽሑፍ ሽልማትን በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ደራሲ መሆኗ አይዘነጋም፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-09
