ሀገሬ ቲቪ

የካንሰር ሕዋሳትን የሚገድለው ቫይረስ

ለመጀመሪያ ጊዜ የሰዎችን የካንሰር ሕዋሳት የሚገድል ቫይረስ ለሰው በመርፌ መሰጠቱን ሰምተናል።

ቫክሲኒያ በሚል የተሰየመው ይህ ሕክምና የካንሰር ሕዋሶችን የመምረጥና የማጥቃት ችሎታ ስላለው ታካሚዎች ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓቸዋል።

መድኅኒቱ ለጥናቱ የመጀመሪያ ተሳታፊ እንደተሰጠ ሜዲካል ኒውስ ቱደይ ጽፏል። ሙከራው በአሜሪካ የሚገኘው የካንሰር ምርምርና ሕክምና ኢንስቲትዩት የሆነው ሲቲ ኦፍ በአውስትራሊያ ከሚገኘው ኢሙጌን ከተሰኘው የባዮቴክ ኩባንያ ጋር በመተባበር እንደተደረገ ታውቋል።

የኒውስዊክ ዘገባ እንዳመለከተው ለሁለት ዓመታት ያህል ሙከራው በመላው አሜሪካ 100 የካንሰር ህመመተኞች ላይ እንደሚደረግ ተሰምቷል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-06-09