ሀገሬ ቲቪ

የጋዜጠኞች ግድያ መበርከት

በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ በመላው ዓለም 24 ጋዜጠኞች ሲገደሉ 293 ጋዜጠኞች ደግሞ ታስረዋል፡፡ ዛሬ የሚከበረውን የሰብዓዊ መብት ቀን በማስመልከት የወጣ ሪፖርት ነው ይህን ያመላከተው፡፡ የጋዜጠኞች ተቆርቋሪ ተቋም ሲፒጄ ዓመታዊ ሪፖርት እንዳመላከተው በ2021 ብቻ ከባለፈው ዓመት በተጨማሪ 13 ጋዜጠኞች በስራቸው ምክንያት ተገድለዋል፡፡ ቻይና 50 ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚ ስትሆን ማይናማር 26 በማሰር ተከታይ ናት፤ከአፍሪካ ደግሞ ግብጽ 25 ጋዜጠኞችን በማሰር ቀዳሚ የዓለማችን ሀገራት ሆነዋል፡፡ ይህ ቁጥር በታሪክ ብዙ ጋዜጠኞች የታሰሩበት ዓመት ሆኖል፡፡ ቬትናም፣ ቤላሩስ፣ ሳዉዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ ቱርክ፣ ሩሲያ፣ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በአንጻራዊነት ብዙ ጋዜጠኞችን በሙያቸው ምክንያት ያሰሩ ሀገራት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በአፍጋኒስታን፣ በሜክሲኮ እና በማይናማር ጋዜጠኞች በዘገባ ላይ እያሉ በጸጥታ ኃይሎች ተገድለው ህይወታቸው አልፏል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1948 የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶችን ያጸደቀው በዚህ ቀን ነው፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-10