ሀገሬ ቲቪ

ፌስቡክ እና የጥላቻ ንግግርን

ፌስቡክ የጥላቻ ንግግሮችን ከይዘቶቹ ላይ የማንሳት ፈተናን መውደቅቁ ተሰማ። ለትርፍ ያልተቋቋሙ ግሎባል ዊትነስ እና ፎክስግሎቭ በተባሉት ቡድኖች የቀረበበትን ፈተና ፌስቡክ ማለፍ አልቻለም።

ቡድኖቹ ኢትዮጵያን መሰረት ያደረጉ የጥላቻ ፅሁፎችን ፌስቡክ ማህበረሰቦችን በሚያገናኘው መድረኩ ላይ ሲተላለፉ እንዳላየ አልፏቸዋል። በኢትዮጵያ በሚገኙ የአማራ፣ ኦሮሞ እና ትግራይ ተወላጆች ላይ ግድያ እንዲፈጸም የሚጠይቅ ሰብአዊነት የጎደላቸው 12 የጥላቻ ንግግር ጽሁፎችን በዚሁ መድረክ ላይ እንዲታዩ አድርጓል።

ኩባንያው ለመለየት እና እንዳይተላለፉ ለማድረግ በጣም ቀላል የነበሩትን እነዚህን ፅሁፎች በዝምታ ማለፉን ቡድኖቹ ኮንነውታል። ፌስቡክ በምያንማር ተመሳሳይ ድርጊቶችን ፈፅሞ ለበርካቶች ሞት ተጠያቂ ሲደረግ ከርሟል፤ በኢትዮጵያ ላይም ከዚህ የተለየ አላደረገም ነው የተባለው።

ፌስ ቡክ በበኩሉ በኢትዮጵያ የሚነገሩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ የይዘት ለዪ ሰራተኞችን ቀጥሬ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ለመከላከል እየሰራው ነው ሲል መልሷል።

ዘገባው ኤ.ቢ.ሲ ኒውስ ነው።

በሳምሶን ገድሉ
2022-06-10