ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ኮንፈረንስ በኢትዮጵያ

ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ልታዘጋጅ እንደሆነ ሰምተናል።

ኮምፍረንሱ ከሰኔ 20 እስከ ድረስ ይደረጋል። ሀገሪቱ ባለንበት ዓመት የካቲት ወር በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አድርጋ አንጋፋውን ዲፕሎማት ዙ ቢንግን መሾሟ ይታወሳል።

ልዩ መልዕክተኛው ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ ቻይና የቀጠናው ሀገራትን የደህንነት፣ የልማት እና የአስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ቁርጠኛ ነች። ኢትዮጵያም በአፍሪካ ቀንድ የቀጣናው መልሕቅ ሀገር በመሆኗ ሰላምን በማስፈን ረገድ ገንቢ ሚና መጫወት እንዳለባት ብለዋቸዋል ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቀተናው ያለው የሰላም እጦት ቻይና በአካባቢው በምታደርገው ኢንቨስትመንት ላይ ስጋቶችን እንደደቀነም ተዘግቧል። ዘገባው የኦል አፍሪካን ኒውስ ነው።

በሳምሶን ገድሉ
2022-06-10