ሀገሬ ቲቪ

‹‹የትራንፕ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ››

የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ አድርገዋል በሚል ተከሰሱ።

ትራምፕ የተከሰሱት ከአንድ ዓመት በፊት ደጋፊዎቻቸው በአሜሪካ ምክር ቤት ወይም ካፒቶል ሂል ከፈጠሩት ግርግር ጋር በተያያዘ መሆኑ ተሰምቷል። የካፒቶል ሂሉን ግርግር ተከትሎ በዴሞክራቶች የሚመራው የአሜሪካ ምክር ቤት ኮሚቴ በማዋቀር ክስ የማሰማት ሂደት ጀምሯል።

ክስ የመስማት ሂደቱ ላይም የግርግሩን ሁኔታ የሚያሳይ ቪዲዮ እና ሌሎችም ማስረጃዎች መቅረባቸው ተነግሯል። ዶናልድ ትራምፕ በ2024 በድጋሚ ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ እንደሚችሉ ፍንጭ የሰጡ ሲሆን ክሱ የፖለቲካ አጀንዳ ያለው የፈጠራ ወሬ ሲሉ አጣጥለውታል።

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-10