በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ግብር ማጣቱን ገለጸ፡፡
የክልሉ የገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ 114 ባለሀብቶች ጠፍተዋል ብሏል፡፡
ከ2010 ጀምሮ እስከ 2014 ባለው ጊዜ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኹለት ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ ገብተው የነበሩ 114 የኘሮጀክት ባለቤቶች ናቸው የጠፉት፡፡
ዋነኛ ምክንያታቸው በክልሉ በነበረው የጸጥታ ጉዳይ ሲሆን በፍላጎታቸው ሥራ አቁመው እንደሄዱ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡
በክልሉ በእርሻ፣ በማዕድን እና በሌሎች ኢንቨስትመንቶች ከዘጠኝ መቶ በላይ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-13
