ሀገሬ ቲቪ

‹‹የህጻናት ሰቆቃ በአፋር››

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) በኢትዮጵያ አፋር ክልል በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከግጭት ሸሽተው ለድርቅ፣ ለረሃብ እና ለከፋ የጤና አገልግሎት እጦት ተጋልጠዋል ይላል ባወጣው መግለጫ፡፡

የቡድን በአዲስ አበባ የድንገተኛ አደጋ አስተባባሪ ራፋኤል ቬችት

“በዚህ ወቅት በጣም የሚያስደነግጠን በጅማሮ ይህንን መማየታችን ነው፡፡በአፋር ክልል ብቸኛው ተግባራዊ ሪፈራል ሆስፒታል በሆነው በዱፕቲ ሆስፒታል ህጻናት በሚያስደንቅ ሁኔታ ረጅም እና አስቸጋሪ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ሲደርሱ እያየን ሲሆን በ48 ሰአት ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ ህመተኞች በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክንያት ለሞት ተዳርገዋል፡፡”

ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የሐኪሞች ቡድኑ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው ሕዝብ፣ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችን ጨምሮ ለዱፕቲ ሆስፒታል የሚያደርገውን ድጋፍ እየጨመ መሆኑን በመግለጫው አትቷል፡፡

በዚህ ዓመት በተቋሙ ውስጥ የገቡት የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህፃናት ቁጥር ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት በሦስት እና በአራት እጥፍ ብልጫ አለው፡፡

የታካሚዎች ሞት መጠን በሚያስገርም ሁኔታ ከፍተኛ ነው፤ በአንዳንድ ሳምንታት ቁጥሩ በእጅጉን አድጎ ከ20 በመቶ በላይ ይሆናል፡፡

ባለፉት ስምንት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 35 ህጻናት የሞቱ ሲሆን፤ከእነዚህም ውስጥ ከሁለት ሦስተኛው በላይ የሚሆኑት በ48 ሰዓት ውስጥ ህይወታቸው አልፏል፡፡

“በግልጽ ለመናገር ከሆነ ይላሉ አስተባባሪው በአፋር የሚኖሩ ብዙ ሰዎች የሰውን ልጅ ህይወት ለማቆየት አስፈላጊ የሆነውን ዝቅተኛውን የጤና እንክብካቤ፣ ምግብ እና ውሃ ማግኘት አልቻሉም፤ ይህንን ለመቋቋም ለተፈናቀሉ ሰዎች እና ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ማህበረሰቦች የምግብ ዋስትና፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና እንክብካቤ፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ውሃ ቁልፍ የትኩረት ነጥቦች በማድረግ ከፍተኛ የሰብአዊ እርዳታ መጨመር ያስፈልጋል፡፡”

በአፋር ክልል ከሚገኙ የጤና ተቋማት ውስጥ 20 በመቶው ብቻ አገልግሎት እየሰጡ ነው ተብሏል፡፡ በዱፕቲ ሆስፒታል ከሚመጡት ህጻናት ከ80 በመቶ በላይ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ሕፃናት ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት የጤና አገልግሎት አልነበራቸውም፡፡

ታካሚዎች ለድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን (ኤምኤስኤፍ) መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን ለማግኘት እንደሚቸገሩ ተናግረዋል፤ ይህም ወደ ከፍተኛ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና ለሕይወት አስጊ የሆኑ ህመሞችን ያስከትላል፡፡

የአንድ ዓመት ልጇን ወደ ዱፕቲ ሆስፒታል ያመጣችው አሲያ ሳሊህ መሀመድ በግጭቱ ብዙ ሰዎች ከአካባቢያቸው መሞታቸውን እና ለደህንነቷ ስትል ከአንድ ወር በላይ በእግር በመጓዝ ተፈናቃዮች ወደሚገኙበት ተቀላቅላለች፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶች እንኳን ማግኘት አለማቻሏን ትናገራለች፡፡

“የምንኖርበት ቦታ በጣም አስቸጋሪ እና ለመኖሪያ የማይመች ነው ፤የሚበላ በቂ ምግብ የለም፣ የሚጠጣ ውሃ የለም፣ የምንኖርበት ቤት ጣሪያ የለውም፣ ስለዚህም ጥላ የለንም እናም ለፀሀይ እንጋለጣለን”

የእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ተጽዕኖ በዱፕቲ ሆስፒታል ውስጥ ባሉ ታካሚዎች ላይ ይታያል ሁለት ሦስተኛው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት ሆስፒታል መተኛት ከሚፈልጉ ቤተሰቦች የተወለዱ መሆናቸውንም መረጃው ይጨምራል።

“በሁለት ቀናት ውስጥ ብቻ 41 ህጻናት በከባድ የሆድ ቁርጠት ወደ ህፃናት ህክምና ሲገቡ አይተናል ምክንያቱም ሰዎቹ የጭቃ ውሃ ለመጠጣት ይገደዳሉ፡፡” ሲሉ ቬች ተናግረዋል፡፡

የሆስፒታሉን የህፃናት ህክምና በትዕግስት መመገብ እና ድንገተኛ ክፍል አቅምን ለማሳደግ፣ አዳዲስ ህንፃዎችን በፍጥነት ለመገንባት እና የውሃ አቅርቦትን እና ንፅህናን ለማሻሻል ከኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ጋር በቅርቡ ስምምነት ላይ መድረሱን ቡድኑ ገልጿል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-13