በንጥረ ነገር የበለፀገ ወይም የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ በደሃ አገሮች ይብዛ እንጂ ችግሩ የምዕራባውያኑም አገሮች ጭምር መሆኑ ይነገራል።
በ2021 በተደረገው ግሎባል ሃንገር ኢንዴክስ ከ116 ሀገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ 90ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧ የተመጣጠነ ምግብ ስለመኖሩ ማሳያ ነው ተብሏል።
የተመጣጠነ ምግብ ባለመመገብ ከ116 ሀገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ 90 ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
የተመጣጠነ ምግብ የሚመገቡ ህጻናት ከ 7 በመቶ አይበልጡም፤
የተመጣጠነ ምግብ የሚመገቡ አዋቂ ዜጎች 16 በመቶ ብቻ ናቸው።
ኢትዮጵያ ለምግብና ሥርዓተ ምግብ ጉዳይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ትኩረት የሰጠችው ቢሆንም አሁንም ግን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት ከሚገባቸው የዕድገት መጠን በታች ናቸው።
ይህ ችግር በሕፃናቱ ላይ መከሰቱ ደግሞ ቀድሞ በአፍላ ወጣቶችና በሴቶች ጤናና አመጋገብ ላይ ያለመሰራቱ ውጤት እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በተለይ በሴቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቀላል እንዳልሆነ ይነገራል።
በትምህርት አቀባበልና በጤና ላይ በሚያደርሰው ጉዳት በተጨማሪ ወደፊት በሚኖራቸው ሕይወት ላይ ጤናማ ልጅ እንዳይወልዱ የሚያግድ ነው።
በጎርጎሮሳውያኑ 2021 በተደረገው ግሎባል ሃንገር ኢንዴክስ ከ116 ሀገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ 90ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧም ችግሩን በግልጽ ያሳያል።
በግብርና ሚኒስቴር የምግብና ስርዓተ ምግብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሃይ ስርጋዌ እንደነገሩን በሀገራችን የተመጣጠኑ ምግቦችን ለመመገብ የሚረዱ በቂ የግብርና ምርቶች አሉ ለማለት ያስቸግራል።
እንደ ወ/ሮ አለምጸሃይ ከሆነ ይህንን ችግር ለመፍታት በማለም ኢትዮጵያ የጤናማ አመጋገብ መመሪያ አዘጋጅታለች። እንደ ዓለም ምግብ እና እርሻ ድርጅት ትርጓሜ ጤናማ የአመጋገብ መመሪያ በሀገራት ውስጥ ጤናማ የአመጋገብ እና የኑሮ ዘይቤ ለመገንባት ይረዳል።
በውስጣቸውም ከስነ ምግብ አኳያ ጠቃሚ የሆኑ ምግቦችን እና አመጋገቦችን በተለያዩ የእድሜ ክልል ለሚገኙ ዜጎቻቸው በምክረ ሃሳብ መልክ የሚያቀርቡበት ነው።
እንደ ድርጅቱ መረጃ በዓለም ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የጤናማ አመጋገብ መመሪያ አላቸው።
ህብረተሰቡ የተመጠጣነ ምግብ የመመገብ የግንዛቤ ችግር አለበት ብለውናል።
ሚኒስቴር ማስሪያ ቤቱ በቂ በጀት እንደሌለው ጠቁመው በሊሎች አለማት እንደለው አይነት ትኩረት ለዘርፉ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
ወ/ሮ ህይወት ዳርስኔ በጤና ሚኒስቴር የብሔራዊ የስርዓተ ምግብ ፕሮግራም አስተባባሪ በበኩላቸው የተመጣጠነ ምግብ የሚመገቡ ህጻናት ከ 7 በመቶ እንደማይበልጡ ጠቅሰው አዋቂዎች ደግሞ 16 ከመቶዎቹ ብቻ እንደሚያገኙ ነግረውናል
ኢትዮጵያ ለሕፃናት በሥርዓተ ምግብና የተመጣጠነ እድገት ላይ የሰጠችውን ትኩረትም ለሴቶችና ልጃገረዶች መድገም እንዳለባት ወ/ሮ ህይወት ተናግረዋል።
አሁን ላይ ያለው 67 በመቶ አዋቂ ሰው በልጅነት ዘመኑ መቀንጨር ያጋጠመው እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-13
