ኬኒያ ከጎረቤቷ ከኡጋንዳ በሚገቡት እንቁላሎች ላይ ቀረጥ ካወጣች በኋላ ሁለቱ ሀገራት ዳግም ወደ ንግድ ጦርነት ሊያመሩ ይችላሉ ተባለ።ካምፓላ እና ናይሮቢ ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት ተከትሎ ባለፈው ታህሳስ ወር ታግዶ የነበረውን ቀረጥ እንደገና በማምጣት ኬንያ ከኡጋንዳ የምታስገባቸውን እንቁላሎች በ 0ነጥብ 6 በመቶ የታክስ መጠን እየቀረጠች ነው ስትል ከሳለች።
የኡጋንዳ ነጋዴዎች ድርጊቱን በመቃወም በሁለቱ ሀገራት መካከል የንግድ ልውውጥ ጥሩ ላይኾን ይችላል ሲሉ ተቃውመዋል።ኹለቱ ሀገራት ምርቴን ንቀሻል በሚል ምክንያት በተዳጋጋሚ ሲካሰሱ ቆይተዋል። በእኛ አቆጣጠር በ2011 ኬኒያ ከኡጋንዳ የሚገባውን ወተት ድርሽ እንዳይልብኝ ማለቷን ተከትሎ ኹለቱ ሀገራት የንግድ ቶርነት ውስጥ ግብተው ነበር።ኡሁንም ታዲያ እንቁላልን ምክን ያት ያደረገው መቃቃር ወደ ጠነከረ ሰጣገባ እንዳይለወጥ ተሰግቷል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-13
