የሴት ልጅ ውበትዋ ጸጉሯ ይባላል በተለምዶ ። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ የሴት ልጅ ውበትዋ ጥፍሯ ወደሚል አባባል እየተቀየረ የመጣ ይመስላል ።
አሁን አሁን ሴቶች ለጥፍራቸው የሚሰጡት እንክብካቤ ጨምሯል ።
ተፈጥሮ ያደላት የራስዋን ጥፍር አስውባ ስትሄድእንዳሰበችው አልሆን ያላት ደግሞ አርቴፊሻል ወይም ሰው ሰራሽ ጥፍሮችን አድርጋ ዝግጅትዋን ታስውባለች ።
ስለ ጥፍር ያነሳንላችሁ ያለምክንያት አይደለም ። አንዲት እንስት ጣት ላይ እያንዳንዳቸው 12 ኢንች ርዝመት ያላቸውን ጥፍሮች ብንመለከት ነው ።
ኮርዴሊያ አዳምስ ትባላለች የ59 ዓመት አዛውንት ስትሆን እ.ኤ.አ. ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ለሰላሳ አመታት ያክል ጥፍሮቿን ሳትቆረጥ ተንከባክባቸዋለች።
ከሰውነቴ አካላቶች ሁሉ ልዩ ትኩረት የምሰጠው ለጥፍሬ ነው የምትለው እንስት ጥፍሮቿን ለመንከባከብ የምታወጣው ወጪ በብዙ ሰዎች ዘንድ ቅሬታን እንደሚፈጥር ትናገራለች ።
አዳምስ ባሳደገቻቸው ጥፍሮች ላይ የተለያዩ መልዕክቶችን ያዘሉ ጥበባዊ ንድፎችን በመሳል በዐለም ላይ ታዋቂ ሆናለች። የተለያዩ ሀገራትም ጥፍሮችዋን እንድታሳይ ጥሪ እንደሚያደርጉላት ትናገራለች ።አዳምስ የእጆቼን ጥፍሮች በማሳደጌ አንዳንድ ሰዎች ያልተገባ ንግግር ይናገሩኛል ። እኔ ግን ውስጤ ያመነበትን ነገር በማድረጌ ክብሬ ይቀንሳል ብዬ አላስብም ትላለች ።
ታዲያ ይህንን የሚያካክሉ ጥፍሮች እጅ ላይ ተቀምጠው እህሉስ እንዴት ይጎረሳል የበርካትች ጥያቄ ነው።
እርሷም ብትሆን በዘመናዊ አለም በመዳፎቻችን እንዳሻን የምንገልጣቸውን ስልኮች መጠቀም ለኔ ብርቄ ነው ትላለች ፤ ያደፉ ልብሶቿንም ማጠብ የህልም ያህል ይርቅባታል። ታዲያ ለእነዚህን ችግሮች እጅና እግሮቿን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። አንድ ነገር ለማድረግ አሰበች ፤ ትምህርት ቤት ለመግባት።
በምዕራባዊያን ዘንድ ለሁሉም ነገር ትምሕርት አለው አዳምስ ጥፍሯን ሳትቆረጥ ህይወቷን እንዴት መምራት እንዳለባት ይረዳት ዘንድ የትምሕርቱን አለም ተቀላቀለች።
አሁን ለ አዳምስ ኑሮ ቀሎላታል ። ልጆቼ ናቸው ምትላቸው ጥፍሮቿ ሳይቆረጡ የቤት ውስጥ ሆኑ የውጭ ስራውቿን እንደልቧ ትከውናለች። ለ 30 አመታት እንደ ልጅ ተንከባክባ ያሳደገቻቸው ጥፍሮች በዓለም ላይ ዕውቅናን ከማስገኘት አልፈው የገቢ ምንጭ ሆነውላታል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-06-13
