ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር ጭምር በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ስትገባ ይታያል።
አሜሪካ ቻይና የታይዋንን ነጻነት እንድታከብር ስትጠይቅ፤ቻይና በአንጻሩ ታይዋንን የግዛቷ አካል አድርጋ ትመለከታታለች፡፡
የቻይና ሕገ መንግሥት አሁንም ድረስ እንደ ቻይና አካል አድርጎ የሚቆጥራት ቢሆንም ከዋናው የቻይና አካል 160 ኪሎ ሜትሮች የምትርቀዋ ደሴት ራሴን የቻልኩ ሉዐላዊት ነኝ የምትል ከእርሷም አልፎ ቫቲካንን ሳይጨምር 13 ሀገራት እውቅና የሰጧት ግዛት ሆና ትገኛለች።
ታይዋን ታዲያ ሉዐላዊ ነኝ ትበል እንጂ በቻይና ተቀባይነትን አላገኘችም ።
ቻይና ከታይዋን ጋር ትብብር የሚያደርጉ ሀገራትን አጥብቃ ትቃወማለች፡፡
አሁን ደግሞ ቤጂንግ አሜሪካ በቻይና ላይ የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨት ስሟን ለማጥፋት ሞክራለች ሲል ከሷል።
የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ዌዪ ፈንጊሄ ከአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ሎልዩድ አውስቲን ጋር ከኢስያ የደህንነት ጉባዔ ጎን ለጎን በሲንጋፖር ተገናኝተው መወያየታቸው ተሰምቷል።
ኦስቲን ቤጂንግ በታይዋን ላይ ተጨማሪ አለመረጋጋትን ከማድረግ መቆጠብ አለባት” ሲሉ የቻይና አቻቸው በበኩላቸው ቻይና “እስከመጨረሻው ትዋጋለች ... መክፈል ያለባትን ማንኛውንም ዋጋ ትከፍላለች” ሲሉ ተደምጠዋል።
የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም እየተነገረ ነው።
የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ዌዪ ፈንጊሄ ሀገራቸው በታይዋን ላይ ያላትን አቋም ተናግረዋል።
“ታይዋንን ከቻይና ለመገንጠል ሙከራ ቢደረግ ሀገራችን ከመታገል ውጭ “ምንም አማራጭ” እንደሌላት መታወቅ አለበት ። ዋሽንግተን ቻይናን ማጥላላቷንና በቻይና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷን እንዲሁም የቻይናን ጥቅምን መጉዳቷን እንድታቆም አሳስባለሁ ።”ዌዪ ፈንጊሄ
በ“አንድ ቻይና” ፖሊሲ ሁሉም የዓለም ሀገራት ማለት ይቻላል ቻይና በታይዋን ላይ ላላት ሉዓላዊነት እውቅና ሰጥተዋል።
አንድ ቻይና ፖሊሲ ማለት "ቻይና" የምትባል አንድ ግዛት ብቻ አልች የሚል አመለካከት ያለው መሆኑ ይታወቃል።
አሜሪካም መርሆውን ትገነዘባለች ነገር ግን ቤጂንግን ለማደናቀፍ ስትሞክር ትትያለች ሲሉ የሀገሪቱ ሹሞች አሜሪካን ይክሷታል።
በተጨማሪም የታይዋን መዲና የሆነችውታይፔን ተገንጣይ ፕሬዝዳንት የምትደግፈው ዋሽንግተን ይህን ፖሊሲ በመጣስ ለደሴቲቱ የጦር መሳሪያ መሸጡን ቀጥላለች ተብሏል።
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዋንግ ዌንቢን ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት አሜሪካ በጣልቃ ገብነት ባህሪዋ አለመግባባቶችን በመፍጠር ፀረ-ቻይና የሀሰት መረጃዎችን እያሰራጨች ነው ብለዋል።
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ጄ. ኦስቲን በሻንግሪ-ላ ውይይት ላይ ባደረጉት ንግግር ቻይናን ወቅሰዋል ።
“ቻይና በምስራቅ ቻይና ባህር እና በደቡብ ቻይና ባህር ላይ ያላትን የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የበለጠ አስገዳጅ እና ጨካኝ ወደ ሆነ አካሄድ እየወሰደችው ነው። በተለይ በታይዋን ላይ እያደረገች ያለችው የተለየ ነው” ኦስቲን
ቻይና በደቡብ ቻይና ባህር ላይ ከሞላ ጎደል ሉዓላዊነቷን ትናገራለች።
ቬትናም፣ ፊሊፒንስ፣ ማሌዢያ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ብሩኒ እና ታይዋን የይገባኛል ጥያቄ አላቸው።
ቤጂንግ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ የይገባኛል ጥያቄዎች ባሏቸው አብዛኛው የምስራቅ ቻይና ባህር ላይ ሉዓላዊነቷን አጥብቃ ትናገራለች።
ቻይና በተለይ ከጃፓን ጋር ለረዥም ጊዜ የዘለቀ የግዛት ውዝግብ ውስጥ ናት።
ሰው በማይኖርበት እና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ አለው ተብሎ በሚታመንበት በጃፓን ሴንካኩ እና በቻይና ዲያኦዩ ደሴት ውዝግቡ ቀጥሏል።
አሜሪካ ከታይዋን ጋር ያላት ይፋዊ ግንኙነት ላይ ገደቦችን እያዘገየች እና ለታይዋን የጦር መሳሪያ ሽያጭ በጥራትም ሆነ በመጠን እያሳደግች ነው በሚል ወቀሳ በርትቶባታል።
ታይዋን ከቻይና ጋር ተባብራ ለመስራት ዝግጁ መሆኗን መግለጿ የሚታወስ ነው ።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-14
