ሀገሬ ቲቪ

“ጋዜጠኞችን ማፈን እየተባለ የሚወራው ተረት ተረት ነው’’

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን 13 መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አከናውኗል። የሕዝብ እንደራሴዎቹ ማኀበራዊ፣ ምጣኔሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ያቀረቡ ሲኾን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ምላሽ ሰጥተውባቸዋል።

ባለፉት አራት አመታት በሀገሪቱ ሰውሠራሽ እና ተፈጥሮአዊ ፈተናዎች ቢያጋጥሙም የተሻሉ ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረዋል። በግብርናው መስክ በርካታ ለውጦች መታየታቸውን የትናገሩት ዶ/ር ዐብይ በቀጣይ ኢትዮጵያ ስንዴ ወደ ውጪ ኤክስፖርት ማድረግ እንደምትጅምር ተናግረዋል።

ህወሓትን አስመልክቶ እየተደረገ ነው ስለተባለው ድርድር እና በተለያዩ ብዙኃን መገናኛ እየተዘዋወረ ስለሚገኘው መረጃ ዕውነታ የተጠየቁት ዶ/ር ዐብይ ምንም ዓይነት የተጀመረ ንግግር የለም ብለዋል። ነገር ግን ህወሓትን ጨምሮ ሰላም ከሚፈልግ አካል ጋር ለመነጋገር ዝግጁ መኾናቸውን ተነግረዋል። ድርድር ሲጀመርም ለሕዝቡ እናሳውቃለን ብለዋል።

ሰላምን በሚመለከት ለሚደረጉ ድርድሮች ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አቶ ደመቀ ሞኮንን የሚመሩት ኮሚቴ መቋቋሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስታውቀዋል። ድርድርን የተመለከት ጉዳይ በዚኹ ኮሚቴ ይደረጋልም ነው ያሉት። ሌላው ጠቅላይ ሚንስትሩ ምላሽ የሰጡበት ጉዳይ በተለያዩ ክልሎች እየተወሰዱ እና መንግሥት የሕግ ማስከበር ስላለው እርምጃ ነው። በተለይም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ እና የክልሉን ነዋሪዎች ሰላም የሚይስደፈርሱ ኃይሎች ላይ እየተወሰደ ስላለው እርምጃ ይኽን ተናግረዋል።

በዚኽ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከተያዙ ሰዎች ውስጥ 3 ሺህ500 የሚሆነው የከዳ ሰራዊት መኾኑንም ዶ/ር ዐብይ ለሕዝብ እንደራሴዎች አስረድተዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲኽ በሀገሪቱ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር እየዋሉ ስላሉት ጋዜጠኞች እና ማኀበራዊ አንቂዎች ጉዳይ ሌላው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የተጠየቁት ጉዳይ ነበር።

በብልጽግና በኩል በሕዝቡን ፍላጎት ለማድመጥ ስንሞክር ሰላም፣ የኑሮ ውድነት እና መልካም አስተዳደር ዋነኛ ጥያቄዎች ሆነው ተነስተዋል። ከሁለት ወር በትፊ በብልጽግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ተሰብስበን፣ ጉዳዮችን ለይተን አውጥተናል። በዚህም በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ቤኒሻንጉል የጸጥታ ሁኔታ፣ በአዲስ አበባ እንዲሁም በሶማሌ ደግሞ አልሸባብና ኮንትሮባንድ ዋነኛ የሰላም እክል ሆነው ተገኝተዋል። ከበ2 ወራት ውስጥ 1000 የሚበልጡ የሸኔ አባላት ርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በተሰራው የሰላም ማስከበር ሥራ በሁሉም ስፍራዎች መልካም ውጤት አግኝተናል። ከዚያ በኋላ መልሰን ሕዝቡን ስናወያይ መልካም ምላሽን አግኝተናል። ርምጃዎች ሲወሰዱ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማስለመድ በተቻለ መጠን ሰላማዊ አማራጮችን ለመከተል ተሞክሯል። ይህም መንግሥትን አቅመ ቢስ አስመስሎታል። ነገር ግን፣ ኃይልን የመጠቀም ስልጣን ያለው መንግሥት እንደ ሆነ መታወቅ አለበት።

በአማራ ክልል በተወሰደው ርምጃ የፌደራል መንግሥት ሳይሆን፣ የክልሉ ልዩ ኃይል ነው የተሳተፈው። የየክልሉን የሕግ ማስከበር ዘመቻ የሚመራው የክልሉ ኃይል ነው፣ ከፌደራል የሚያገኘው የቴክኒክ ድጋፍ ብቻ ነው።

ርምጃው አካባቢያዊ መሆኑን፣ በሕዝብ ጥያቄ እንደ ተጀመረ፣ በተገኘው ውጤት ሕዝብ ደስተኛ መሆኑን እና ሰላም እያገኘ መሆኑ መታወቅ አለበት። በሀገር ወዳዶች ስም የሚቆሙ አጥፊዎችን ለሕግ ማቅረብ ግዴታ ነው። በክልሉ በሕግ ማስከበር ርምጃ 3500 የከዳ ሰራዊት ተይዟል፣ ከዚሁም ውስጥ ከ2000 የሚበልጠው ከልዩ ኃይል የወጣ ነው።

ሃሺሽ፣ የውጪ ምንዛሬ፣ ተቀጣጣይ ፈንጂ እና ቦንብ ይዘናል። ከዘመቻው በኋላ የገባ እና መከላከያ ብቻ የሚታጠቀው አዲስ አይነት ጠመንጃ አለን። መከላከያን ገድለው ያንን ጠመንጃ ታጥቀው የተገኙ ሰዎች ናቸው የተያዙት። እሳት ቤት እንዳያጠፋ ሰብሰብ ተደርጎ መያዝ አለበት። ነጻነትና ብልጽግና የሚኖረው ከመረጋጋት ጋር ነው።

በስህተት የተያዘ፣ ያለአግባብ የተጎዳ ሰው ሊኖር ይችላል። ተጣርቶ የእርምት ርምጃ ሊወሰድ ያስፈልጋል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-06-14