ከአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ በአስር ወራት 418 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የተገኘው ገቢ ካለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ102 ሚሊየን ዶላር ጭማሬ አሳይቷል፡፡
ገቢው ወደ ውጭ ከተላከ 146 ሺሕ 342 ቶን ምርት የተገኘ ሲሆን፤ የተላከው የምርት መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ17 ሺሕ 634 ቶን ጭማሬ ማስመዝገቡን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከጨርቃ ጨርቅና አልባሳት 153 ሚሊዮን ዶላር፣ ምግብና መጠጥ 93 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዶላር፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች 33 ሚሊዮን ዶላር፣ ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች 22 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር፣ ማምረቻው ዘርፍ፣ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ 16 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር እና ሥጋና ወተት አፈፃፀም 98 ሚሊዮን ዶላር ድርሻ አላቸው፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-14
