ሀገሬ ቲቪ

በጋንቤላ የተፈጠረው ግርግር

በጋምቤላ ከተማ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ክልሉ አስታወቀ፡፡ ግርግሩ የተነሳው መንግሥት ሽብርተኛ በተባለው በሸኔ ወታደሮች እና በጋምቤላ ነፃነት ግንባር መካከል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በጋምቤላ ከተማ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ 30 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት የቆየ ሲሆን የመንግሥት ኃይል ባካሄደው ትግል ከተማውን በከፊል ነፃ ማውጣት ተችሏል፡፡ የደረሰው ጉዳት በውል ባይታወቅም በሁለቱም ወገን ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል፡፡

በዮሴፍ ከበደ
2022-06-14