አማዞን በሰው አልባ አውሮፕላኖች እቃዎችን ቤት ለቤት ማድረስ ሊጀምር ነው፡፡
ኩባንያው በዚህ ዓመት መጨረሻ 4 ሺሕ ዜጎች በሚኖሩባት በካሊፎርኒያ ሎክ ፎርድ እሽጎችን ለገዢዎች በሰው አልባ አውሮፕላኖች ማድረስ እንደሚጀምር ተናግሯል፡፡
አውሮፕላኖቹ ከእይታ መስመር ባሻገር መብረር የሚችሉ ሲሆን አውሮፕላኖችን፣ ሰዎችን፣ የቤት እንስሳትን እና እንቅፋቶችን ለማስወገድ ሴንሰር ተገጥሞላቸዋል፡፡
ቸርቻሪው ዓላማችን ከአንድ ሰዓት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ጥቅሎችን ለደንበኞች በደህና ማድረስ ነው ብሏል፡፡
ከዚህ ቀደም በቀድሞ አለቃ እና መስራቹ ጄፍ ቤዞስ አማካኝነት በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ በርካታ ሰውአልባ አውሮፕላኖችን ወደ ስራ ለማስገባት ቢታቀድም አለመሳካቱ አይዘነጋም፡፡
ኩባንያው በየዓመቱ ወደ 470 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገቢ ያገኛል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-14
