ሀገሬ ቲቪ

“ለድርድር ተዘጋጅተናል”- የትግራይ ኃይሎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጦርነቱ በሰላም ያብቃ ባሉ ማግስት የትግራይ ኃይሎች ለድርድር ዝግጁ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ ጦርነቱን በሰላም ለማብቃት ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ በትግራይ በኩል ከመንግሥት ጋር ከ18 ወራት በላይ ሲያደርጉት የነበረውን ጦርነት ለማብቃት በኬንያ መንግሥት አሸማጋይነት በሚካሄድ ድርድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ተብሏል፡፡

በህወሓት ሊቀመንበር እና በክልሉ ፕሬዝዳንት ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የተሰራጨው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም ለድርድር ያቀረባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች አላካተተም፡፡

በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ የሚችል ከፍተኛ የመልዕክተኞች ቡድን ወደ ኬንያዋ መዲና ናይሮቢ ለመላክ ዝግጁ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ድርድሩ በኬንያ መንግሥት መሪነት የአፍሪካ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት፣ አሜሪካ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ተሳታፊ እንዲሆኑም ጠይቋል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-15