ቡና በየቀኑ መጠጣት አጣዳፊ የኩላሊት መቁሰል አደጋን ይቀንሳል ይላል የሳይ ቴክ መረጃ፡፡
በመካከለኛ ዕድሜ ላይ ከሚገኙ 14ሺሕ 207 ተሳታፊዎች በተሰራው ጥናት ውስጥ በየቀኑ ቡና የሚጠጡ ሰዎች በ 5 በመቶ ለአጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ሲሆን ፤በቀን ከሁለት እስከ ሦስት ስኒ የሚጠቱት ደግሞ ከፍተኛ ደረጃ የመጋለጥ እድላቸው ዝቅተኛ ነው ተብሏል፡፡
በዳሰሳ ጥናቱ ወቅት ቡና ፈጽሞ የማይጠጡ 1 ሺሕ 694 ሰዎች አጣዳፊ የኩላሊት ጉዳት ተመዝግቧል፡፡
ቡና ከኩላሊት በተጨማሪ የስኳር በሽታ፣ የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች እንዲሁም የጉበት በሽታዎችን ለመከላከል ወሳኝ ነው ይላሉ በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ትምህርት ቤት የኒፍሮሎጂ ክፍል ዳይሬክተር፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-15
