ሀገሬ ቲቪ

ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ ኬሚካሎች መዘዝ

5ሚሊዮን የሚሆነው የዓለማችን ህዝብ በአደገኛ ኬሚካሎች ምክንያት ህይወቱ እንደሚያልፍና ከዚህም ውስጥ 70 ከመቶ የችግሩ ሰለባዎች ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት እንደሆኑ የአለም ጤና ሚንስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በሀገራችን እትዮጵያም ለግብርና፤ለተባይና ለአረም ማጥፍያ ፤ ለተለያዩ አገልግሎቶች ወደ ሀገር ዉስጥ የሚገቡ እነኚሁ ኬሚካሎች የጉዳት መጠናቸዉ ስር እየሰደደ መምጣቱን ነው የጤና ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይንስና ቴክኒዮሎጂ ለባለድርሻ አካላት በጋራ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅኁፍ ላይ ያስታወቁት፡፡

በተለይ ለግብርና ምርቶችና ለቤት ዉስጥ የምንጠቀማቸዉ ኬሚካሎች ከፍተኛ የሆነ ያቀማመጥና የአጠቃቀም ችግር እንደሚሰተዋልባቸው በጥናቱ ተገልፀዋል፡፡

በነኝህ አደገኛ ኬሚካሎች ምክንያት በጤናና በአከባቢና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰ መምጣቱ አንዱ የጥናቱ ግኝት መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ባለሙያዎቹ፤ችግሩ አፋጣኝ እርምጃ ካለተወሰደበት ቀጣዩን ትዉልድ ጭምር መቅጠፉ አይቀሬ መሆኑንም ያሳስባሉ፡፡

እሰከ 2030 ችግሩን ለመቆጣጠር እቅድ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን፤ ለዘላቂ መፍትሔዉ ግን ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት፤የግንዛቤ ማስጨበጡን ስራ ማጠናከር፤የቁጥጥር ስራዎች መስራትና ሌሎችም ተግባሮች ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑም ተነግሯል፡፡

በቦጋለ ተስፋዬ
2022-06-16