ሀገሬ ቲቪ

በደሴ የወደመው የመድሐኒት አቅራቢ ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በምስራቅ አማራ ትልቁ ማከፋፈያ የሆነው የደሴ ቅርንጫፉ መውደሙን ገለጸ፡፡ ቅርንጫፉ ለ 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሕዝብ የሚያገለግል እንደነበር የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አወል ሀሰን ተናግረዋል፡፡ ቅርንጫፉ በአካባቢው ለ27 ሆስፒታሎች፣ ለ303 ጤና ጣቢያዎች እና ለ60 ወረዳዎች የመድኃኒት እና ሌሎች የህክምና ግብዓት በማቅረብ አገልግሎት እየሰጠ ነበር፡፡ የሕወሓት ኃይሎች በቅርንጫፉ በክምችት የነበሩ መድኃኒት እና ሌሎች የህክምና ግብዓቶችን ዘርፈዋል፡፡ በተጨማሪም ሊዘረፉ የማይችሉ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱም ተጠቁሟል፡፡ ቡድኑ በከፍተኛ መዋለ ንዋይ የተገነባ ግዙፍ የእናቶች እና ህፃናት ክትባት ግብዓት ማከማቻ የማቀዝቀዣ ሰንሰለት መጋዘን፣ ዋና መጋዘን ፣ ቢሮዎች፣ የማከማቻ መሰረተ ልማት፣ ፎርክሊፍቶች ፣ የደህንነት መቆጣጠሪያ ስርዓቶችን እንዲሁም የቢሮ መሳሪያዎችን ጭምር አውድሟል ፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-10