የዓለም ራስ ምታት ኾኖ የቀጠለው ኮቪድ 19 ቫይረስ እስካኹን ከ6 ሚሊዮን በላይ ለሚኾኑ ሰዎች ሞት ምክንያት ኾኗል። ይኽ አስከፊ ወረርሽኝ መላ ሳይገኝለት ‘’ሞንኪ ፖክስ’’ አሊያም የዝንጀሮ ፈንጣጣ የተባለ በሽታ በተለያዩ ሀገራት ተከስቷል።
አኹን ላይ 39 ሀገሮች ይኽ ቫይረስ ሀገራችን ገብቷል ሲሉ አሳውቀዋል። ከነዚኽ ሀገራት ውስጥ ስምንቱ ደግሞ ከአህጉራችን የሚመዘዙ ሀገራት ናቸው።
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሞኢቲ ቅዳሜ እንደተናገሩት ከስምንቱ ሀገራት ስድስቱ ቀደም ሲል በቫይረሱ የተያዙሰዎችን አግኝተናል ሲሉ ሪፖርት ያደረጉ ናቸው ብለዋል።
በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ቀዳሚዋ ናይጄሪያ እስካኹን 36 ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ ተይዘውብኛል ብላለች። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 10 ተጠቂዎችን ይፋ ስታደረግ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ደግሞ 8 የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተጠቂዎችን ይፋ አድርገዋል። ቤኒን ካሜሮንም በተመሳሳይ ቫይረሱን አግኝተናል ሲሉ ይፋ ያደረጉ ሀገራት ናቸው።
ከዚኽ ቀደም ስለቫይረሱ ምንም ያላሉት ጋና እና ሞሮኮ አኹን ላይ ሪፖርት ማድረጋቸው ታውቋል። ከነዚኽ ሀገራት ውጪ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስን እስካሁን አግኝተናል ሲሉ ሪፖርት ባያደርጉም ጥርጣሬ አለን ሲሉ ግን ያሳወቁ ሀገራት መኖራቸው ተዘግቧል። እነዚኽ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሴራሊዮን፣ ሱዳን እና ኡጋንዳ ናቸው።
ኹኔታው ያልተለመደ ነገር ግን ብዙ ሀገሮችን እያስጨነቀ ያለ ነው ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሞኢቲ ተናግረዋል።
በኮቪደ 19 ወቅት እንደታየው በሕክምና ኾነ በክትባት ክፍፍል ወቅት እንደታየው ያልተገባ አድሎ እንዳይፈጠር እንደአህጉር በቂ ዝግጅት ማደረግ እንደሚያስፈልግም ዳይሬክተሯ ተናገረዋል።
በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ሀገራት የምርመራ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።
አዲስ እና ደኀንነቱ የተጠበቀ የፈንጣጣ ክትባት 85 በመቶ የዝንጀሮ ፈንጣጣ መከላከል ችሏል። ገር ግን ነገር ግን የተባበሩት መንግስታት የጤና ኤጀንሲ በአሁኑ ጊዜ የጅምላ ክትባትን አልመከረም።
“ስሞልፖክስ” የተሰኘውና አዱሱን ቫይረስ መከላከል ይችላል የተባለው ክትባት በዘመቻ መልክ መሰጠት ከተጅመረ ለአፍሪካ ቅድሚያ እንዲሰጥ ተጠቁሟል።
የምስራቅ አፍሪካ ማኀበረሰብ በቀጠናው ያሉ ሀገራት በተጠንቀቅ ቆመው ቫይረሱን እንዲከላከሉ አሳስቧል። በተጨማሪ ሰዎች ስለ ቫይረሱ ምንነት እና እራሳቸውን እንዴት መከላከል እንዳለባቸው እንዲኹም ቫይረሱ እንዳይዛመት አስፈላጊውን መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው ብሏል።
ከዚኽ ቀደም ከ 1 ሺህ 500 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከአፍሪካ ሪፖርት የተደረግ ሲኾን ከ 60 በላይ የሚኾኑት ደግም በዝንጀሮ ፈንጣጣ ሕይወታቸው አልፏል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-20
