በዘመናችን በፊልም ጥበብ እውን እንዲመስሉን ተደረገው የሚሰሩ አስፈሪ ፊልሞች አሉ። ለዛሬ ግን ወደ 1967 መለስ እንላለን። ጃውስ የተሰኘ ፊልም በዛሬዋ እለት መለቀቁ ብዙዎችን ወደ ውሃ ስፍራ ለመሄድ ፍርሃት እንዲያድርባቸው ምክንያት ሆኗል። ፊልሙ ለ27 አመቱ ወጣት ዳይሬክተሩ ተጽእኖ ፈጣሪነቱ ከፍ እንዲል አድርጓል።
ፊልም ላይ የተመረኮዘ ታሪክን ለመዳሰስ 47 አመታትን መለስ ልንል ነው። በዛሬዋ እለት ስቴቨን ስቲልበርግ የተሰኘ ሰው ዳይሬክት ያደረገው ጃውስ (Jaws)የተሰኘ ፊልም በቴያትር ቤቶች ለእይታ በቃ። ይህ ፊልም ግን ለብዙዎች ወደ ውሃ ስፍራዎች ለመሄድ የፍርሃት ምንጭ ሆነ። በዚህም የፊልም በሰዎች ስሜት ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ አሳይቷል።
አንድ ሪዞርትን ስላሸበረ ነጭ ሻርክ የሚያትተው ፊልሙ በጊዜው ከፍተኛ ገቢ ማስገባት የቻለ ፊልም መሆን ችሏል። በአካዳሚ የፊልም ሽልማት ላይ ታጭቷል። ሶስት ኦስካርንም በምርጥ የፊልም ኢዲቲንግ፣ በምርጥ ኦሪጂናል ነጥብ እና በምርጥ ድምጽ ዘርፍ መውሰድ ችሏል። የ27 አመት እድሜ ለነበረው ለዳይሬክተሩ ስፒልበርግም በርካታ ተከታታይ ፊልሞችን ፈጥሮለታል።
በጊዜው በ486 ሲኒማ ቤቶች መታየት የቻለው ፊልሙ በ78 ቀናት ውስጥ የጊዜው ትልቁ ፊልም ሆነ። ዳይሬክተሩ ስቴቨን ስፒልበርግ የፔተር ቤንችሌይ ጃውስ ልቦለድን መሰረት አድርጎ ልብ አንጠልጣይ ፊልምን ለአለም ተመልካቾች አደረሰ።
በመጀመሪያዎቹ 78 ቀናት ከ"The Godfather’’ ከፍተኛውን ቦታ በመንጠቅ በ460 በላይ ቲያትር ቤቶች ተስተናግዷል።
በ1960ዎቹ ተሰርተው እውቅ መሆን ከቻሉ ፊልሞች አንዱ የሆነው ጃውስ የፊልም ስክሪፕቱ የተጻፈ የነበረው ወጣት በነበረው የፊልሙ ዳይሬክተር ስቲልበርግ እና ካርል ጎትሊብ ነበር።
ይሄው የሳይንሳዊ ልቦለድነት አስፈሪ ዘውግ ያለው ፊልም የሎንግ ደሴት የክረምት ሪዞርት ላይ መቸቱን አድርጓል። ሰዎች ከግዙፍ ተፈጥሮ ሻርክ የገጠማቸውን ፈተና በማስቃኘት ይፈሳል።
ይሄው አካሄዱ ነው ታዲያ በብዙ የፊልሙ ተመልካቾች ላይ ወደ ውሃማ ስፍራ የመሄድ ፍርሃትን ያሳደረባቸው።
በማሳቹሴት በማርታ ቬንያርድ የተቀረጸው ፊልሙ በውቅያኖስ ላይ የተቀረጸ የመጀመሪያ ዋነኛ ፊልም ነው። በዚህም ከታለመለት በጀት እና ጊዜ በላይ ፈጅቷል። የቴክኒካል ችግሮች የመካኒካል ሻርኮች ብልሽት ጭምር አጓቶታል። የቀረጻ ጊዜውም ከ55 ቀናት ወደ 159 ቀናት ተጓቷል።
በተመልካቾች ላይ የስሜት ጫና ማሳደር የቻለው ብሎም በድምጹ እና በፊልም ኤዲቲንግ ስራው የኦስካር ሽልማትን ማግኘት የቻለው ይሄው ፊልም በ1960ዎቹ መጨረሻ የእይታ ቀዳሚነቱን በመያዝ የታይም መጋዚን የፊት ገጽ እስከመሆን በቅቷል።
ለሁለት አመታት ያክልም ቀዳሚ ገቢ ያስገኘ ፊልም መሆን ችሏል። ለ27 አመት ዳይሬክተሩ ስቲልበርግ በሆሊውድ የዳይሬክተርነት ቦታ እንዲያገኝም ምክንያት ሆኗል። ይሄው ፊልም ዳይሬክተሩ ስፒልበርግን በጊዜው ተደማጭ ከነበሩ የፊልም ዳይሬክተሮች አንዱ አድርጎታል።
ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማግኘት የቻለው ፊልሙ በተለቀቀ በ38 ቀናት ውስጥ 2.5 ሚሊዮን ቲኬቶች ለተመልካቾች ተሸጠውለታል። በጊዜው ከፍተኛ ወጭ በሚባል 12 ሚሊዮን ዶላር ፊልሙ በሪቻርድ ዛኑክ እና ዴቪድ ብራውን ቡድኖች ተሰርቷል።
በአብርሃም በለጠ
2022-06-20
