የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ለአፍሪካ ኀብረት ባደረጉት ንግግር አፍሪቃ የሩስያ ጦርነት ታጋች ናት ብለዋታል።
ሩሲያና ዩክሬን ጦርነት መግጠማቸውን ተከትሎ የጦርነቱ አበሳ ለአፍሪካም የተረፈ ነው ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል።
ይኽን ሊሉ የቻሉበት ምክንያት ደግሞ የዩክሬን ወደ ውጭ የምትልከውን ምርት በመዝጋቷ የእህል እና የማዳበሪያ እጥረት በማስከተሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ለረሃብ አደጋ በመጋለጣቸው ነው ብለዋል።
የዓለም መረጋጋትን ወደነበረበት ለመመለስ "አስቸኳይ ውይይት ያስፈልጋል" ሲሉ የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሳፋኪ ተናግረዋል።
ምዕራባውያን አገሮች ሩሲያ የዩክሬንን ሰፊ የእህል ማከማቻ እንድትለቅ እያሳሰቡ ይገኛሉ። የሩሲያ ጦር በወደቡ መስፈር የምግብ ዋጋ በእጅጉ እንዲንር ምክንያት እንደኾነ ነው ቢቢሲ የዘገበው።
ዘለንስኪ በውይይታቸው ወቅት እንደተናገሩት ከኾነ በዩክሬን ጥቁር ባህር ወደቦች ውስጥ በሩሲያ ጦር የተያዙትን የእህል ማከማቻዎች ለማስለቀቅ መንግሥታቸው "ውስብስብ ሲሉ የጠሩትን ድርድር" እያደረገ ነው ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም "ይህ ጦርነት ለእርስዎ እና ለአገሮችዎ በጣም ሩቅ ሊመስል ይችላል ነገር ግን በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ያለው የምግብ ዋጋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአፍሪካውያንን ደጅ እያንኳኳ ነው ሲሉ ለአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሳፋኪ አስረድተዋል።
“በግዛታችን ላይ ጦርነት በከፈቱት በእነርሱ አፍሪካ ታግታለች ። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በጀመረችው ጦርነት። ይኽ ጦርነት ለእርሶ ሀገራት የራቀ ሊኾን ይችላል ነገር ግን የምግብ ዋጋ መናር በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአፍሪካ ቤተሰቦችን ቤት አንኳኩቷል።”
የዘለንስኪ እና የአፍሪካ ኀብረት ንግግር ለመጀመሪያ ጊዜ ለአህጉራዊው አካል ንግግር ለማድረግ ከጠየቁ ከ10 ሳምንታት በኋላ የተደረገ ውይይት ነው።
ቢቢሲ አግኘሁ እንዳለው መረጃ ከኾነ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከአፍሪካ ኀብረት አባል ሀገራት ጋር ለሚያደርገው የበይነመረብ ውይይት 55 የሀገር መሪዎች የተጋበዙ ቢሆንም አራት ብቻ ተገኝተዋል።
የተቀሩት አገሮች ተወካዮች ልከዋል ሲል ዘግቧል።
በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የአፍሪካ ሀገራት የተለያየ አቋም ይዘዋል።
የተባበሩት መንግሥታት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችው ወረራ መኾኑን በመግለጽ ይኽንን ለማውገዝ ባሰባሰበው የሀገራት ድምጽ 17 የአፍሪካ ሀገራት ድመጸ ተአቅቦ አድርገዋል።
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማኪ ሳል ሚስተር ዘለንስኪን ለህብረቱ ንግግር ስላደረጉ አመስግነዋል።
አፍሪካ የአለም አቀፍ ህግ ደንቦችን፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና የንግድ ነፃነትን ለማክበር ቁርጠኝነቷን ቀጥላለች" ሲሉ ማኪሳል ተናግረዋል።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ሚስተር ሳል ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተው ነበር።
በውይይታቸውም ወቅት አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ በሁለቱ ሀገራት ጦርነት ምንም የማይመለከታቸው ንጹሀን አፍሪካውያን እየተጎዱ ነው ሲሉ ማኪሳል ተናግረዋል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-21
