በትምህርት ቤቶች ለተጀመረውን የምገባ ፕሮግራም የዓለም የምግብ ፕሮግራም ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባሳለፍነዉ ሳንት መጨረሻ በኢትዮጵያ የዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ክላውዴ ጂቢዳር ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው ይኽን የጠየቁት።
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በአዲስ መልክ የተጀመረውን የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም በሁሉም ክልሎች እንዲስፋፉ ድጋፍ ያድርግልን ብለዋል።
በተጨማሪ ሚኒስትሩ በትምህርት ዘርፉ የትምህርት ጥራት መሻሻያ ሪፎርሞች መጀመራቸውን እና በትምህርት ቤት ምገባ ዙሪያም እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች ማስረዳታቸውን ከትምህርት ሚንስቴር የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-21
