በ3 መስሪያ ቤቶች ከውዝፍ ያልተሰበሰበ ከዘጠኝ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መኖሩ ተሰማ።
በገቢዎች ሚኒስቴር ፣ በጉምሩክ ኮሚሽን እና በሌሎች መስሪያ ቤቶች 9 ቢልዮን 527 ሚልዮን 539 ሺህ 626 ብር ከውዝፍ ያልተሰበሰበ ገቢ መኖሩ መረጋግጡን ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጸዋል።
የዋና ኦዲተር መ/ቤት ለምክር ቤቱ ባቀረበው ሪፖርት 24 መሥሪያ ቤቶች በልዩ ልዩ የሒሳብ መደቦች ሳያስፈቅዱ እና በጀት ሳያዛውሩ ከመደበኛ በጀት ብር 645 ቢሊዮን 198 ሚሊዮን927 ሺህ44 ከተደለደለው በጀት በላይ ወጪ የሆነ ሒሳብ መገኘቱንም አረጋግጧል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-21
