
ግዙፉ አለም አቀፍ የዲጂታል ግብይት ቴክኖሎጂ ድርጅት የሆነው አማዞን አገልግሎቱን በአፍሪካ የማስፋት እቅድ እንዳለው ተገለጸ።
እንደ ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘገባ ድርጂቱ አገልግሎቱን ሊያሰፋ ካሰበባቸው ሃገራት ደቡብ አፍሪካ እና ናይጀሪያ ይገኙበታል።
የማስፋፋት እቅዱም በ2023 ተፈጻሚ ይሆናል።
በቀጣዩ አመት ተቋሙ ከአፍሪካ ውጭ ባሉ ሃገራት በቤልጅየም፣ ቺሊ እና ኮሎምቢያም አገልግሎቱን ለማስፋት ማቀዱ ተሰምቷል።
በአብርሃም በለጠ
2022-06-21