ሀገሬ ቲቪ

ረጅም ጆሮዋ ያላት ፍየል ተወለደች

በተፈጥሮ ከታደሉት አካል በተለየ አፈጣጠር ወደዚህ ዓለም የመጡ እንስሳትን የተለየ ተብለው ሲነገርላቸው እንሰማለን። ከወደ ፓኪስታን አንዲት ፍየል ከተለመደ የፍየሎች የጆሮ መጠን ከፍ ያለ ጆሮን ታድላለች መባሉን ሰምተናል።

የፓኪስታንዋ ካራቺ ግዛት አሁን አይን እና ጆሮ መሳብ ጀምራለች። ሙሀመድ ሀሰን ናሬጆ ደግሞ የዚህች ፍየል ባለቤት ነው። ሰኔ 5 ከወደ ጋጣው እናት ፍየል አንዲት ባለቤቷ ሲምባ ሲል የጠራትን ግልገል በሰላም ትገላገላለች። ሙሀመድ ወደ ጋጣው ሲደርስ ባየው ነገር ይገረማል። ሲምባ ከቁመቷ በላይ የሆነ 46 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ጆሮን ተሸክማለች።

እንደፍየል ላሉ ፍጥረታት ይህ አዲስ ነገር ነው። ባለረጅም ጆሮዋ ግልገል አሁን በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ ስሙን ለማፃፍ ጥረት እየተደረገ ነው።

በፓኪስታን ውስጥ ፍየሏ አሁን ዝንዋ ናኝቷል። የመገናኛ ብዙኃኑም የፊት ገፃቸው ማድመቅመቂያ አድርገዋታል። ይህችው ግልገል ገና መራመድ ስትጀምር እንደ አንገት ልብስ ትከሻዋን አልፎ የተንዘረፈፈው ጎሮዋ መሪአቱን እየጠረገ ይከተላታል።

እንደ የዜና ተቋሙ ቴሌግራፍ ከሆነ የፍየል ረዣዥም ጆሮዎች የጂን ሚውቴሽን ወይም የጄኔቲክ መታወክ ውጤቶች ናቸው። ፍየሊቱም ታዲያ ዘርፋፋው ጆሮዋ የተስማማት ይመስላል።

የዚህች ፍየል ባለቤቶችም ተስፋን ጥለዋል፤ ግልገላቸው በዓለማችን ባለረጅም ጆሮ የፍየል ግልገል ተብላ እንደምትጠራ። ፍየሏ ታዲያ ኑቢያ የተሰኘ የፍየል ዝርያ ናት።

እነኚህ የፍየል ዝርያዎች በረጃጅም እን አበተንዘረፈፉ ጆሮዎቻቸው የሚታወቁ ናቸው። የእነዚህ ዝርያዎች ጆሮ መርዘም ያለምክኛት እንዳልሆነ ጥናቶች ያስረዳሉ። በሞቃታማ አካባቢ የሚኖሩት እነዚህ እነዚህ ዝርያዎች የረዘመው ጆሯቸው የሰውነታቸውን ሙቀት ለመቆጣጠር እና ለመቀዝቀዝ ያግዛቸዋል።

በእነዚህ ዝርያዎች መስፈርት እንኳ ቢለካ የዚህችው ሲምባ የተሰኘችው ፍየል ጆሮዎች ርዝመታቸው የበዛ ነው። በግዛቲቱ በበጋ ግዜ ሙቀቱ እስከ 47 ዲግሪ ሴልሺየስ ይደርሳል፤ ታዲያ ይህችው ፍየል እድለኛ ነች ሙቀቱን የመቋቋም አቅምን ታድላለች እየተባለታት ነው።

ኤክስፕረስ የተባለ የዜ ወኪል እንደዘገበው ፣ ፓኪስታን 54 ሚሊዮን የሚጠጉ ፍየሎችን በውጧ ይዛለች። ይህም በዓለማችን ትልቋ የፍየል ሀገር አሰኝቷታል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-06-21