በቼም ጆሮ አይሰማው የለ።
በቀደሙት ዘመናት ገዥ እና ሻጭ ገበያ ወጥተው ሲገበያዩ፤ ሻጩ ለያዘው ንብረት በምትኩ ሌላ ረብ ያለው ንብረትን ይቀበላል።
ይህ አይነቱ የገበያ ስርዓት አሁን ባለንበት ዘመን ከተረሰሳ ግዜያትን ተሻግሯል።
ታዲያ አንድ የቻይና ቤት ገንቢ ኩባንያ እንዴት ተደርጎ ይረሳል ያለ ይመስላል።
ኩባንያው ገንብቼ ለሚሸጣቸው ቤቶች ስንዴን እንደ ክፍያ መቀበል ጀምሬአለው ብሏል።
የሀገሬ መገናኛ ብዙኃን ታዲያ ተስፋ የቆረጠው የቤት ገንቢ ስንዴን በቤት ሊለውጥ ነው ሲሉም ተደምጠዋል።
ኩባንያው ታዲያ ቤቶቹን በሚገነባበት ማዕከላዊ ሄናን ግዛት ያሉ ገበሬዎችን ሊላማ ያደረገ እቅድ እንደሆነ እየተናገረ ይገኛል።
ኩባንያው ያወጣው ማስታወቂያ እንዲህ ይላል “ስንዴን ለቤት መግዣ ያውሉ”።
ታዲያ በግዛቲቱ የሚገነቡት ቤቶች ወደ 600 ሺህ የሚጠጉ ናቸው።
ይህ አይነቱ የመሸጫ መንገድም ለተወሰኑ ቀናት ብቻ የሚቆይ ነው ተብሏል።
ከዚህ ቀደም በማዕከላዊ ቻይና ያሌ ሌላ የቤት አልሚ እየገነባቸው ያሉ ቤቶችን በነጭ ሽንኩርት ቀይሩኝ ሲል ማስታወቂያ አስነግሮ ነበር።
የቤት አልሚው ማስታወቂያውን ባስነገረ 16 ቀናት ውስጥ ብቻ 852 ሰዎች በመገንባት ላይ ያሉትን ቤቶች ጎንኝተዋል።
30ዎቹ ደግሞ በነጭ ሽንኩርት ግብይታቸውን ፈፅመዋል።
የነጭ ሽንኩርት እና የስንዴ ዋጋ በቻይና ለ500 ግራም 1.5 ዩውን ያስከፍላል።
የኮቪድ 19 በዓለም ላይ መከሰት የቻይናን ኢኮኖሚ ጎድቶት ቆይቷል።
በ2022 ቻይና የኢኮኖሚ እድገቷ 5.5 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።
ታዲያ በሀገሪቱ የሚገኙ የቤት ገንቢዎች ገዢዎችን ይስብልናል ያሉትን ዘዴዎች ለመጠቀም እየሞከሩ ይገኛሉ።
አንዳንዶቹ የቤቶቹን እድሳት በነፃ እናደርጋለን እስከማለት የደረሰ።
አልረጋጋ ያለው የቻይና ኢኮኖሚ በርካታ የቤት ገንቢዎችን ጭንቀት ጭምሯል።
ከጭንቀታቸው ተንፈስ ያደርጋቸው ዘንድ ታዲያ አነስተኛ የቅድመ ክፍያዎችን፣ ለገዢዎች የገንዘብ ድጎማዎች እንዲሁም ከአንድ በላይ ልጅ ላላቸው ቤተሰቦች የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን የሚያስገኙ የግዢ አማራጮችን እየተጠቀሙ ይገኛል።
በሳምሶን ገድሉ
2022-06-22
