
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የወርቅ አምራቾችን ለማበረታታት ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ የ35 በመቶ ጭማሪ አድርጎ ለመግዛት ወሰነ፡፡
ባንኩ የወርቅ የኮንትሮባንድ ንግዱን ለመቆጣጠር ከመጋቢት 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከዓለም አቀፍ የወርቅ ገበያ ላይ እንደ ወርቁ ብዛት ከአስር በመቶ እስከ 29 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ይገዛ እንደነበር አስታውሷል፡፡
ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ ከወርቅ ግብይት 1 ነጥብ 2 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አግኝቷል፡፡
በተያያዘ ባለፉት 11 ወራት ከወርቅ ምርት 513 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስትር አሳውቆል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-22