
የኬንያ ሆስፒታል ኩላሊታቸዉን ለመሸጥ የሚጠይቁ ሰዎች ጥያቄ መጨመሩን ተከትሎ ኩላሊት አንገዛም ሲል ማስታወቂያ አወጣ፡፡
የኬንያታ ብሔራዊ ሆስፒታል በፌስቡክ ገፁ የመልዕክት ሳጥን ዉስጥ ከሚመጡ ጥያቄዎች መካከል ኩላሊቴን በስንት ትገዛላችሁ የሚለዉ ይበዛል ብሏል፡፡
ለሆስፒታሉ እየቀረበ ያለዉ ጥያቄ በኬንያ በምግብ እና በነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የተነሳ ነዋሪዎች ላይ የተስፋ መቁረጥ እርምጃ መሆኑን አመላካጭ ነው ተብሏል፡፡
ሆስፒታሉ የአካል ክፍሎን መሸጥ በጥብቅ የተከለከለ እና ህገ-ወጥ ተግባር መሆኑን ያስተውሉ ፤በነጻ ፈቃድ ብቻ ነው መለገስ የሚችሉት ሲል ምላሽ እየሰጠ ነው፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-22