ሀገሬ ቲቪ

ዳግም ወደ ውጪ ጉዳይ የተመለሱት አምባሳደር

በኬንያ ለሦስት ዓመታት የኢትዮጵያ አምባሳደር ኾነውያገለገሉት አምባሳደር መለስ ዓለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይና የአስቸኳይ ሁኔታዎች መከታተያ ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው ተሹመዋል፡፡

አምባሳደር መለስ ዓለም ወደ ኬኒያ ከማቅናታቸው በፊት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ነበሩ። ከአኹን ቀደም የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ደግሞ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው መሾማቸው ታውቋል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2022-06-22