ኢትዮጵያ ጥንታዊት ሀገር እንደ መሆኗ በርካታ የሚዳሰሱ ብሎም የማይዳሰሱ ቅርሶች ይዛለች ይሁን እንጂ እነዚህን ቅርሶች በተለያየ ጊዜያት በስጦታም ይሁን በዝርፊያ ከሀገር ውጥተው ገሚሶቹ በሙዚየም አንዳንዶቹ በብይነ መረብ ለግብይት የሚቀርቡ ሲሆን የተቀሩት የት እንደደረሱ እንኳን አይታወቅም።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማህበረ ቅዱሳን በተለያዩ ጊዜያት የተዘረፉ ቅርሶችን ማስምልሰን ዓላማው አድርጎ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰኔ 18 ምክክር አድርጓል።
በመድረኩ የቀረበው ጽሁፍ እንዳመላከተው ቅርሶች የቱሪዝም መስህቦች ሲሆኑ ኢትዮጵያ ከምታገኘው ከቱሪዝም መስህብ ውስጥ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅርሶችን በማስጎብኘት የሚገኘ ነው።
ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኗ ቅርሷን በአግባቡ ያለመጠበቋ ያስወቅሳታል ታደሰ ዓለሙ (ዶ/ር) የማኅበረ ቅዱሳን የቅርስና ቱሪዝም አገልግሎት ክፍል ኅላፊ ሲሉ ተናግረዋል።
የሰሜን ጦርነትን ተከትሎ በርካታ ቅርሶች ከሀገር በሕገወጥ መንገድ በመውጣት ለገበያ እየቀረቡ መሆኑም ተገልጾል።
ቅርሶች እንዴት ይዘርፋሉ በሚል ከቤቱ ከተነሱት ሃሳቦች ድህነት፣የህግ ማዐቅፍ ጉድለት ፣ቸልተኝነት እና መሰል ችግሮች ናቸው።
በቅርስጥበቃ ባለሥልጣን በውጪ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ቅርሶች ከ8 ሺሕ በላይ ቢሆኑም በማህበሩ በኩል ደግሞ 11 ሺሕ በላይ ቅርሶች ተገኝተዋል።
ከእነዚህም ውስጥ ክብረ ነገስት ፣የታሪከ መጽሕፍት፣ የብራና ጥቅል እና ድጉስ መጽሕፍት፣የነገስታት የክብር አልባሳት እና መስል ቅርሶች ይገኙበታል።
በተለያዩ ሀገራት በርካታ መጽሃፍት ሲኖሩ በዋናነት በፈርንሳይ 970 በላይ ፣በእንግሊዝ 1 ሺሕ50 ፣ በጣሊያን 1 ሺሕ 290 በጀርመን 931 ፣በእስራኤልና በቻይና በርካታ ጽላቶች እና መጽሕፍት በቅርቡ ትገኘተዋል።
ቅርስን የመጠበቅ ብሎም የማስመልስ ስራ በአእምሮዋችን ያለ ሥራ ነው የሚሉት ደግሞ ዶ/ር መስከረም ሊቺሳ ናቸው።
ማህበሩ፣የቅርሰ ጥበቃ ባልሥልጣን ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣በውጪ ያሉ ግለስቦች እና መሰል ተቋማት በጋራ ሊሰሩበት እንደሚገባ ተገልጾል።
በቀጣይ እንዲህ ያለውን ውይይት በማዘጋጀት የተዘርፉ ቅርሶችን ለማስመልስ ላሉትም ጥበቃ የማድርግ ኅላፊነት የሁሉም መሆኑን በመገንዘብ በጋራ መስራት ላይ ማትኮርን አላማ አድርጎል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-27
