ሀገሬ ቲቪ

ለዩኒቨርሲቲዎች የጥንቃቄ ማሳሰቢያ ተሠጠ

የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተማሪዎችና የዩኒቨርሲቲ ማህበረስብ አባላት ጥንቃቄ አድርጉ አለ።ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህውሃት ቡድን የሚደግፋቸው የብዙሃን መገናኛ የመማር ማስተማር ሂደት ለማደናቀፍ ተማሪዎች በብሄርና በሃይማኖት በመከፋፈል ግጭት እንዲፈጠር እየሰሩ እንደሆነ ደርሼበታለሁ ብሏል።

ሰሞኑን «በአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ የኦሮሞ እና የሌሎች ብሄር ተማሪዎችን ለማጥቃት የተደራጀ የደህንነት ቡድን ወደ አማራ ክልል ተልኳል» የሚል በዩኒቨርሲቲዎች ግጭት ለማስነሳት መልዕክት አስተላልፈዋል ስለዚህ ተማሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጉ ብሏል።

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-27