በከተማዋ የሚስተዋለውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር በዘላቂነት ለመቅረፍ የተጀመረው ፕሮጀክት መጠናቀቁ ተነገረ። ይኽው ፕሮጀክት ከ1መቶ 62 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ የተከናወነ ነው ተብሏል።
የበጀቱ 15 በመቶ በተቋሙ የተሸፈነ ሲሆን፤ ቀሪው 85 በመቶ ከቻይና መንግስት ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር ነው፡፡ ፓወር ቻይና የተባለ የቻይና ኩባንያ በጥቅምት 2009 ዓ.ም የተጀመረ ነበር። 107 ነጥብ 7 ኪ.ሜ የመሬት ውስጥ ተቀባሪ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣ 69 የመካከለኛ መስመር መቆጣጠሪያ፣ ከመሬት በላይ 600 ኪ.ሜ የሚሸፍን የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ተሠርቷል
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-27
