
የአፍሪካ ኅብረት በትላንትናው ዕለት ከሞሮኮ ወደ ስፔን ሜሊላ ለመሻገር ሲሞከሩ ሕይወታቸው ባለፈ ስደተኞች ላይ አፋጣኝ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ።ሲጂቲኤን 23 ስደትኖች መሞታቸውን ሲዘግብ ፕረስ ቲቪ ደግሞ 37 ናቸው ብሏል።
የስደተኞቹ ሕይወት ያለፈው የድንበሩን አጥር አልፈው ወደ ስፔን ለመግባት በሞከሩ እና አጥሩን ታልፉና እርምጃ እንወስዳለን ባሉ የጸጥታ አካላት መሀከል በተፈጠረ ጸብ እንደኾነ እየተነገረ ነው።
ሌላው ደግሞ ወደ ስፔን ሜሊላ ለመሻገር ሙከራ ያደረጉ ከ2 ሺህ የሚበልጡ ስደተኞች በመገፋፋታቸውና በመረጋገጣቸው ነውም እየተባለ ነው።የአፍሪካ ህብረት ዋና ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ክስተቱን ክብረነክ ነው ብለውታል።
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-27