ሀገሬ ቲቪ

የግብጽ አዲሱ ከተማ 70 በመቶ ተጠናቀቀ

ግብጽ ከዋና ከተማዋ ካይሮ በስተ ምስራቅ 50 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኝ እና በ40 ሺህ ሔክታር ላይ እየገነባኹት ያለው አዱሱ ከተማዬ 70 በመቶ ተጠናቆልኛል አለች።

በከተማዋ ከ70 እስከ 90 በመቶ የሚሆነው የ10 የመኖሪያ አካባቢ ግንባታ ተጠናቋል። መንግሥታዊ ተቋማት የሚገኙበት፣ የንግድ እና የፋይናንስ ጨምሮ በርካታ ግዙፍ ፕሮጀክቶች እየተጠናቀቁ ነው ተብሏል።

ሀገሪቱ እንደዚህ ዓይነት ግዙፍ ከተማ ለመገንባት ያሰበችው ከ 100 ሚሊዮን ሕዝቧ አንድ አምስተኛው በዋና ከተማዋ ካይሮ በተጨናነቀ ኹናቴ እየኖረ በመኾኑ ነው ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-06-27