ሀገሬ ቲቪ

አሜሪካ የህውሓት ጥቃትን ማውገዝ

አሜሪካ የህወሓት ታጣቂዎች የፈፀሟቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አሳስበውኛል አለ፡፡ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በሰጡት መግለጫ ነው ይህ የተገለጸው፡፡ የባይደን አስተዳደር የህወሓት ታጣቂዎች በአማራ እና አፋር ክልሎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያደረሷቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የግፍ ድርጊቶች እንዲሁም በተቋማት ላይ ያደረሷቸው ውድመቶች እንዳሳሰበው ገልጿል፡፡ አሜሪካ ድርጊቱን እንድታወግዝ በሀገር ቤት እና በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በተለያየ መንገድ ሲጠይቁና ግፊት ሲያደርጉም መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ አሜሪካ ለተጎጂዎች ያልተገደበ እርዳታ ሊደርስ እንደሚገባ ተነግሯል፡፡ ከሚቀርቡት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መካከል ሰዎችን ያለ ፍርድ መግደል፣ ጾታዊ ጥቃቶችን ማድረስ እና የሰብዓዊ እርዳታ ተጎጂዎች ጋር እንዳይደርስ መከልከል የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-13