የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ልኡካን ቡድን በቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ በዓል ላይ ለመገኘት ሮም ገቡ።
የጥንቱን የቤተክርስቲያን ወግ በመከተል በካቶሊክ እና በኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ሕብረት የበለጠ ለማጠናከር በሊቀጳጳሳት የሚመራ የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ ልኡካን ናቸው ሰኔ 22 2014 ዓ.ም.በሮም በሚከበረው የቅዱሳኑ በዓል ላይ የሚገኙት ሲል ቫቲካን ዜና አገልግሎት አሳውቋል።
ቡድኑን የሚመራው በብፁዕ አቡነ ኢዮብ የቴልሚሶስ ሊቀ ጳጳሳት ሲሆን ከሀሊካርናሰስ ኤጲስ ቆጶስ አድሪያኖስ እና ፓትርያርካዊ ዲያቆን በርናባስ ግሪጎሪያዲስ ይገኙበታል። ሐሙስ ከብፁዕ ወቅዱስ ርእሰ ሊቃነጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-28
