የቡና ልማትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ምርታማነቱን ለማሳደግ 14 ሚሊዮን ዮሮ ወይንም የ769 ሚሊዮን ብር በጀት የተያዘለት “ኢዩ ካፌ” የተሰኘ ፕሮጀክት በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።
ኘሮጀክቱ በኢትዮጵያ በሚገኙ አምስት ክልሎች በኦሮሚያ ፣ በአማራ ፣ በደቡብ ፣ በሲዳማ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ዋና ዋና የቡና አብቃይ በሆኑ 28 ወረዳዎች ይተገበራል ተብሏል።ኘሮጀክቱ ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በቡና ማልማት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እንዲሠሩ እንዲሁም የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-28
