
የአፍሪካ ልማት ባንክ ለክትባት 3 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ። ባንኩ በአህጉሪቱ ያለውን የክትባት ጥገኝነት ለማስወገድ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውጥን ይዟል።
እቅዱ በሩዋንዳ ዋና ከተማ ኪጋሊ ላይ የተመሰረተ አዲስ የምርምር፣ ልማት እና የማምረቻ ማዕከልን ያካትታል።
አፍሪካ በውጭ ልገሳ ላይ ያላትን ጥገኝነት ለማቆም ይረዳል ተብሎም በሰፊው ተወድሷል። አፍሪካ በአሁኑ ወቅት ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑ መድሃኒቶችን ወደ ሀገር ውስጥ እንደምታስገባ እና በየዓመቱ 14 ቢሊዮን ዶላር እንደምታወጣ ይታወቃል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-28