የአውሮፓ ህብረት የታዳሽ ሃይልን ድርሻ በጎርጎሳውያኑ 2030 ወደ 40 በመቶ ለማሳደግ ማቀዱ ተሰምቷል።
የአውሮፓ ህብረት የኢነርጂ ሚኒስትሮች የታዳሽ የኃይል ምንጮችን እንደ የፀሐይ እና የንፋስ ኃይልን ድርሻ ለማሳደግ ከስምምነት መድረሳቸው ነው የተነገረው።
በሉክሰምበርግ የተሰበሰቡት የኢነርጂ ሚኒስትሮችም ከ2020 አሃዝ ጋር ሲነጻጸር የአውሮፓ ህብረትን አጠቃላይ የሃይል ፍጆታ በ2030 ቢያንስ በ9 በመቶ ለመቀነስ አልመዋል ሲል ሲጂቲኤን ጽፏል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-28
