ሀገሬ ቲቪ

<<ከብልጽግና ጋር የጌታ እና ሎሌ ግንኙነት አይኖረንም>> አቶ አንዱዓለም አራጌ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትሕ(ኢዜማ) በ1ኛ መደበኛ ጉባኤ የከፍተኛ ኃላፊነት ቦታዎች ምርጫ ለማካሄድ የእጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ዛሬ መጠናቀቁን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

ምርጫውን ተከተሎ ፓርቲው ተከፍሏል በሚል በርካታ ወሬዎች ቢናፈሱም በውስጣችን የሃሳብ ግጭት እንጂ ልዩነት የለንም ብሏል።

አቶ ሐብታሙ ኪቲባ የፓርቲው ዕጩ ም/መሪ በፓርቲ ውስጥ የከፍተኛ ኃላፊነት ቦታዎች ምርጫ በኢትዮጵያ ያልተለመደ መሆን ሕዝቡ ብሎም አባላትን እያደናገረ ነው ብለዋል።

ወደ ውድድር ለመግባት ዋነኛወው ምክንያት መሰረታዊ የሃሳብ ልዩነቶች ናቸው ብለዋል የፓርቲው ዕጩ መሪ አቶ አንዱዓለም አራጌ።

በተለይ 6ተኛው ምርጫ፣በሰሜን ጦርነት እና ከመንግሥት ጋር ያለው ግንኙነትን በተመለከተ ሰፊ ልዩነት በመንጸባርቁ ለምርጫው መነሻ ሆኖል።

በምርጫ ቅስቅሳ ወቅት ገዢው ፓርቲ ብልጽግና የማህበራዊ ሰራዊት ከፍተኛ የስም ማጠልሸት እና ምርጫውን የማሰናክል ስራ እየስሩ እንደነበር ፓርቲው በመግለጫው አብራርቷል።

በሰኔ 25 እና 26 በ1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ምርጫው በአባላት የሚደርግ ሲሆን በህጋዊ መንገድ ተመራጩን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን አቶ ሐብታሙ ኪቲባ ገልጸዋል።

ፓርቲው ሲመሰረት ጀምሮ የያዛቸውን ስትራቲጂካዊ እቅዶች ሰላም እንዲሰፍን፣ፓርቲውን ማጠናከር ፣ምርጫ ማሸነፍ፣በሕዝብ ተቀባይንትን ማግኘት የሚለው ግቦች ውጤት አልባ ሆነዋል ተብሏል።

በሌላ በኩል ከብልጽና ጋር በጋራ ለመስራት ሲወሰን በጉባኤው 7 ነጥቦች ቢቀመጡም አንዳቸውም ተግባራዊ አልሆኑም፤ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ ጥቂት አባላት በመንግሥት መዋቅር ውስጥ መኖራቸው ብቻ አብሮ መስራትን አያመላክትም ሲሉ ይወቅሳሉ።

“ፓርቲው ከዚህ በኋላም ቢሆን ከብልጽግና ጋር የሚኖረው ግንኙነት የጌታ እና የሎሌ አይሆንም” ብልዋል።

አቶ አንዱዓለም አራጌ በመጪው ቅዳሜና እሁድ የከፍተኛ ኃላፊነት ቦታዎች ምርጫ በ1ኛ መደበኛ ጉባኤ ይከወናል ተብሎ ይጠበቃል።

በፍሬሕይወት ታደሰ
2022-06-29